ቻን፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጎል የማያገባበት ውድድር?
ጥር 10, 2008

በይርጋ አበበ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ወይም ካፍ የአህጉሩን እግር ኳስ ለማሳደግ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚወዳደሩ ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድናቸውን ወክለው የሚወዳደሩበት የእግር ኳስ ውድድር አዘጋጀ። ውድድሩንም ቻን ብሎ የጠራው ሲሆን በየሁለት ዓመቱ እንዲካሄድ በቆረጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሩዋንዳ እየተካሄደ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በዚህ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መሳተፍ የቻለው ከሁለት ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ ተዘጋጅቶ በነበረው ሶስተኛው የቻን ዋንጫ ወቅት ነበር።

በሶስተኛው የቻን ዋንጫ የተሳተፈው ብሔራዊ ቡድንም በወቅቱ የመጀመሪያውን ማጣሪያ የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር መጫወት ባለመፈለጉ በፎርፌ ያለፈ ሲሆን ሁለተኛውን የማጣሪያ ጨዋታውን ደግሞ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጫውቶ አንድ እኩል ከተለያየ በኋላ በመለያ ምት ነበር። በዘንድሮው ውድድር ለተሳትፎ የደረሰው ደግሞ በመጀመሪያ የኬኒያን ብሔራዊ ቡድን ሁለት ለአንድ አሸንፎ እና በቀጣዩ ጨዋታ ደግሞ የብሩንዲ አቻውን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት በውድድሩ ላይ ሶስቱንም ጨዋታ ተሸንፎ አንድም ጎል ማስቆጠር ሳይችል ከምድቡ አራተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ካፍ የመደበለትን የ100 ሺህ ዶላር ጉርሻ ይዞ ነበር የተመለሰው። በወቅቱ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውም “አጥቂው ጎል አላገባልኝ ካለ ፍርድ ቤት አላቀርበው” ሲሉ አወዛጋቢ እና የተጫዋቾቻቸውን ክብር የሚነካ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። በዚያ ውድድር ከዋልያዎቹ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለው የነበሩት የሊቢያ እና የጋና ብሔራዊ ቡድኖች ለፍጻሜ ቀርበው በመለያ ምት ሊቢያ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችላለች።

በሶስተኛው የቻን ዋንጫ ከምድቡ ማለፍ የተሳነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ከነበረው የቡድኑ ስብስብ መካከል ሶስቱን ብቻ ማለትም አዲስ ህንጻ ሳላዲን ሰይድ እና ሽመልስ በቀለን ሳይዝ የተጓዘ በመሆኑ ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ቡድን ነበር። ዳሩ ግን በወጣቶች የተገነባው እና በአገሪቱ የሰላም አየር መተንፈስ ያልቻለው የሊቢያ ብሔራዊ ቡድን የዋንጫው ባለቤት ሆነ። 
በዘንድሮው ውድድር ደግሞ ዋልያዎቹ በምድብ ማጣሪያው እንደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካሜሩን እና አንጎላ ጋር በሞት ምድቡ ውስጥ መደልደላቸው ይታወሳል። ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ሩዋንዳ ሲያቀናም ከምድቡ የማለፍ እድል የሌለው እንደሆነ አሰልጣኙ ማመን ቢከብዳቸውም ፌዴሬሽኑ ግን ለተሳትፎነት የዘለለ ቆይታ እንደማይኖረው በልቡ ያወቀው ይመስላል። ለዚህም የብሔራዊ ቡድኑ ከሩዋንዳ የመመለሻ ጊዜውን የሚያመለክተው የአውሮፕላን ቲኬት የተቆረጠው ቡድኑ ሶስተኛውን የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ባደረገ በማግስቱ እንደሆነ ያመለክታል። ይህ ማለት ደግሞ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ “እቅዳችን የቻልነውን ሁሉ አድርገን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ነው” ቢሉም ፌዴሬሽኑ ግን ከተሳትፎ የዘለለ ቆይታ እንደማኖረው አመላካች ሆኗል።

አሁን ጥያቄው ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ወይም አለማለፉ አይደለም። ነገር ግን በአራት ተከታታይ የቻን ጨዋታዎች ብሔራዊ ቡድኑ እንዴት አንድ ጎል ማስቆጠር ይሳነዋል? የሚለው ነጥብ ነው። ትናንት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር በተካሄደው ጨዋታ ከጠንካራ ክለቦቿ ተጫዋቾቿን ያዋቀረችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮንጎ በብሔራዊ ቡድናችን ላይ የጨዋታም የጎልም የበላይነቱን ወስዳ አምሽታለች።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአጥቂዎች ደረጃ የወረደ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም ቢያንስ አንድ ጎል እንኳ ማስቆጠር እንዴት እንደተሳናቸው አነጋጋሪ ሆኗል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mali [765 days ago.]
 Lengeru sheba ateki eko new yezen yehedenew ababa Tafese

Bereket (Beka) [764 days ago.]
 ሰውነት ቢሻው ጀግናችን ነው ማንም ያልሰራውን ታሪክ ሰርቷል ይህ ሰው ለናሽናል ቲማችን እንደገና ያስፈልገናል:: ፌዴሬሽኑ ሰውነት ቢሻውንና ስዩም ከበደን አስማምቷቸው እንደገና ለናሽናል ቲማችን ቢሾማቸው እርግጠኛ ነኝ ብሔራዊ ቡድናችንን ትልቅ ቦታ ያደርሱታል:: ካልሆነ ደግሞ የዩጋንዳው ናሽናል ቲም ኮች የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አሰልጣኝ ሚቾን ለብሔራዊ ቡድናችን ቢሾም ቡድናችንን ይለውጠዋል !!!

bikila [762 days ago.]
 please coach yohnnis sahli will out of the scuad with out any prevellage please return back sewunet bishaw he was the hero of Ethiopian foot ball history.that was right he won south Africa olaying more nigereia and what ever.we love SEWUNET BISHAWWWWWW.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!