ካሜሩን የዋልያዎቹን ቀጣይ ጉዞ ይወስናሉ
ጥር 12, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ አመሻሹ ላይ ከካሜሩን አቻው ጋር የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ያካሂዳል። ብሔራዊ ቡድኑ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ በቻን ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያውን ዋንጫ ካነሳው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጫውቶ ሶስት ለባዶ መሸነፉ ይታወሳል። ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከካሜሩን አቻው ጋር በሚያካሂደው ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት ካልቻለ ከምድቡ መውደቁን በጊዜ የሚያውቅ ይሆናል ማለት ነው። የካሜሩን ብሔራዊ ቡድነ በበኩሉ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ የአንጎላን ብሔራዊ በቡድን አንድ ለባዶ በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ይህም ከምድቡ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ እንዲቀመጥ አድርጎታል። ለመሆኑ ዋልያዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፋቸውን የመጀመሪያ ውጤት ዛሬ ማስመዝገብ ይችላሉ? የሚለውን ሃሳብ ከዚህ በታች እንመለከታለን።

ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ አስፋጊነት

በቻን ውድድር ላይ የተሻለ ጉዞ ማድረግ በአንድ በኩል የብሔራዊ ቡድኑን ሞራል ከመገንባቱ አኳያ መልካም የሚባል እድል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ፌዴሬሽኑ ከካፍ የሚያገኘውን ጉርሻ ዳጎስ እንዲል ያደርግለታል። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ውድድሩን ፊፋ እውቅና ስለሰጠው በዚህ ውድድር የሚመዘገቡ ውጤቶች በፊፋ ወርሃዊ የብሔራዊ ቡድኖች ደረጃ ላይ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ብሔራዊ ቡድኑን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ የአገሪቱ ወርሃዊ ደረጃ በየወሩ ወደታች የሚጓዝ ሲሆን በዚህ ውድድር ከሚያካሂዳቸው ሶስት የምድብ ጨዋታዎች መካከል ቢያንስ አንድ ወይም ሁለቱን ማሸነፍ ከቻለ በአንድ በኩል ከምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ለማለፍ ከፍተኛ አጋጣሚ የሚፈጥር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከምድቡ በማለፉ ብቻ የደረጃ ማሻሻያ ሊያገኝ የሚችልበት እድል ሰፊ ይሆናል።

በዛሬው ጨዋታ ሊመዘገብ የሚችለው ውጤት እና የተጋጣሚ ቡድን ደረጃ

ከአንድ ዓመት በፊት አካባቢ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድነ ከካሜሩን አቻው ጋር ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የግጥመ ማጣሪያ ውድድር ሲደለደል በርካቶች የአሸናፊነቱን ግምት ያለ ምንም ማመንታት ለምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ሰጥተው ነበር። ሆኖም በደርሶ መልስ የተመዘገበው ውጤት እውነታ ኢትዮጵያዊያኖቹ እንስቶች በተጋጣሚያቸው ላይ የበላይ ሆነው ያጠናቀቁበትን ውጤት ነበር።

በወንዶች ብሔራዊ ቡድን የሁለቱ አገራት የእግር ኳስ ደረጃ ለየቅል ቢሆንም ዛሬ የሚካሄደው የቻን ዋንጫ የምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታም በርካቶች የአሸናፊነቱን ግምት ለካሜሩን ብሔራዊ ቡድን እንደሚሰጡ ሳይታለም የተፈታ ነው። ሆኖም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድናቸውን በሚገባ ማደራጀት ከቻሉ እና ካለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች ስህተቶቻቸው ትምህርት ወስደው መጫወት ከቻሉ ሊመዘገብ የሚችለው ውጤት ለዋልያዎቹ ተስፋ ሰጭ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ባለፉት ሁለትና ከዚያ በላይ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ከአሰልጣኙ ላይ የታዩት ታክቲካል ስህተቶች በዛሬው ጨዋታም ብሔራዊ ቡድኑን ዋጋ የሚያስከፍሉ ሊሆኑ እንዳይሆኑ ሊታሰብበት ይገባል።

ከመጀመሪያው የምድቡ ጨዋታ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እና አምበሉ ስዩም ተስፋዬ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ፕረስ ኮንፈረንስ ላይ ውጤቱ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ መሆኑን ተናግረው ነገር ግን ደጋፊያችንን ለመካስ በቀጣዮቹ ጨዋታ ተስተካክለን እንገባለን ብለው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ “ተጫዋቾቼ የነገርኳቸውን ታክቲክ አልተገበሩልኝም የበረኛ ችግርም ነበረብን” ሲሉ መናገራቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ምክንያቱም አሰልጣኙ እንደተናገሩት ተጫዋቾቻቸው የአሰልጣኛቸውን ቃል መተግበር ካልቻሉ በተለያዩ ጊዜያት የቡድናቸውን አምበል ወይም ቲም ማን ጠርተው መናገር ሲገባቸው እሰሳቸው ግን ከመቀመጫቸው አልተነሱም ነበር። በዚያ ላይ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የነበረባቸውን ድክመት በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ መቀየር አልቻሉም ነበርና ነው።

የአሰልጣኙ ደካማ ታክቲክ

አሰልጣኝ የአንድ ቡድን ውጤት መሰረት መሆኑ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም እያስመዘገበ ላለው ውጤት መወቀስ ካለበትም ሆነ መመስገን ካለበት ውዳሴም ነቀፋውም የሚያቀናው ወደ አሰልጣኙ ይሆናል። በዚህም መሰረት ዋልያተጨዎቹ ባለፉት ሶስት እና አራት ወራት እያስመዘገቡ ላሉት ደካማ ውጤት ያለ ምንም ጥርጥር የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ደካማ ታክቲክ ነው። አሰልጣኙ ቋሚ ቡድን ከመገንባት ይልቅ በየጊዜው ቡድናቸውን ሲያዋቅሩ እና የተለያየ የአጨዋወት ሲስተም ሲከተሉ ይታያሉ። በተለይ በዚህ የቸቻን ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ እንደ ጋቶች ፓኖም አይነት አማካይ ተከላካይ እያለው ተስፋዬ አለባቸውን እና አስራት መገርሳን የጠራ ሲሆን በተለይ ሁለቱን ተጫዋቾች ማለትም ተስፋዬን እና ጋቶችን በአንድ ጊዜ በማሰለፍ አጨዋወታቸውን ወደ 4 2 3 1 በመቀየር ለመተግበር ሲሞክሩ ታይተዋል። ይህ የጨዋታ ሲስተም በዓለም እግር ኳስ በስፋት እየተዘወተረ ያለ አጨዋወት ቢሆንም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ግን ውጤታማ ሊሆን አይችልም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በመጀመሪያ ደረጃ ብቁ የሆነ አጥቂ ብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ የለም። ብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ብቁ አጥቂ አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን የተጋጣሚ ቡድን ተከላካዮችን የሚያስጨንቅ አጥቂም የለም እንደ ሙሉዓለም ጥላሁን አይነት ታጋይ አጥቂ ቢኖርም እንኳ አሰልጣኙ የመጀመሪያ ተመራጭ ያደረጉት ቆሞ መጫወት የሚወደውን ታፈሰ ተስፋዬን ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአሰልጣኙ ታክቲክ የማይጠቅም ይሆናል ማለት ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋዬም በቦታው ጥሩ የሚባል ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ቀስቃሽ ሲፈልግ ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋዬም ሆነ ጋቶች የሚነጥቋቸውን ኳሶች በሚገባ ለቡድን ጓደኞቻቸው በትክክል ማቀበል ላይ ያላቸው ሪከርድ በጣም ደጋማ ነው። በዚህ በኩል በተለይ ጋቶች ለቡድን አጋሮቹ ከሚያቀብላቸው ኳሶች ይልቅ ለተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾች የሚሰጣቸው ኳሶች ይበዛሉ። ተጫዋቹ ይህንን ስህተቱን በብሔራዊ ቡድን ላይ ብቻ ሳይሆን በክለብ ፉትቦሉም በተደጋጋሚ ሲፈጽም የሚታይ ሲሆን ክለቡን በርካታ ጊዜያት ዋጋ አስከፍሎታል።

የተዘነጋው ታደለ እና አስታዋሽ ያላገኘው ሳምሶን

ሳምሶን ጥላሁንም ሆነ ታደለ መንገሻ በክለቦቻቸው የሚያሳዩት ብቃት በአገሪቱ ደረጃ ጥሩ ተጫዋች የሚያስብላቸው ነው። በዚህ የተነሳ ሳይሆን አይቀርም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድናቸውን ሲያዋቅሩ ሁለቱን የቀድሞ የፈረሰኞቹ ሰልጣኞች በቡድናቸው ስብስብ ውስጥ ያካተቷቸው። ነገር ግን ታደለም ሆነ ሳምሶን በበቂ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፈው አገራቸውን ማገልገል ሲችሉ አልታዩም። ለዚህ ደግሞ የአሰልጣኙ ድክመት ሲሆን በተለይ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዶ በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ሁሉንም ተጫዋቾቻቸውን አሰልፈውቅ ማየት እየቻሉ አሰልጣኙ ግን ተጫዋቾቹንብ በተለይም ሳምሶን ጥላሁንን ከተጠጠባባቂ ወንበር ውጭ አድርገውት ታይተዋል። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም በተጫዋቾቹ ላይ እምነት በማጣታቸው ሩዋንዳ ላይ ሊጠቀሙባቸው ያልቻሉት።

አሰልጣኙ በአሁኑ ሰዓት ኤሊያስ ማሞንም ሆነ ጋቶች ፓኖምን ወይም በሀይሉ አሰፋን እና ራምኬል ሎክን በቋሚነት ከመጠቀም ይልቅ እንደ ታደለ መንገሻ እና ሳምሶን ጥላሁን አይነት ተጫዋቾችን እድል ቢሰጧቸው ውጤት መቀየር ባይችሉ እንኳ ቀደም ሲል ብሔራዊ ቡድኑ ይታወቅበት የነበረውን መልካም የኳስ ቅብብል ማሳየት ይችሉ ነበር። በዚያ ላይ አስራት መገርሳንም ሆነ ታፈሰ ሰለሞንን የመጠቀም ፍላጎት ቢኖራቸው መልካም ይሆናል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Habetom [694 days ago.]
 በጣም የሚያሳፍር አቃጣይ አሰልጣኝ ቢኖር ዮሃንስ ነው ከጨዋታው በፊት አጥቅቶ እንደሚጫወት ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ሲሰብከን ሲነግረን ነበር ግን በተቃራኒው ሲከላከልና ልክ እንደ ካሜሮን ቡድን የመጀመሪያውን ጌም እንዳሸነፈ አቻ ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያሳልፈው ቡድን ሲከላከል ሰዓት ሲያባክን ነበር :: ትልቁ የዮሃንስ ችግር ልጆቹን እንዴት አድርጎ መጠቀም እንዳለበት አላወቀም አያውቅምም እንጂ ካሜሮን ከባድ ቡድን አይደለም :: ኧረ ኮች ሰውነት ቢሻው ጀግናው ይግደለን ለእነ ናይጄሪያ ለእነ ደቡብ አፍሪካ ራስ ምታት የሆነ ቡድን ሰርቶ እኮ ነው ያኮራን :: እድሜህ ይባረክ ጋሽ ሰውነት ቢሻው !!!

bikila [694 days ago.]
 how can we kepping result from this team? you know guys who is the attaker of the team?tafese.tafese was the patriot of the past generation not now.so from this old man do you need goal?kikikikiki hahahahahahah amazing sory yohannis you are not a coch but you are a politician please out from the truck and join the poletics please.

bikila [694 days ago.]
 Tekebreshi yenorshiwu duro besegele: Mechawecha aregeshi yohanis sahle. zeraf

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!