የሳላዲን ማረፊያ የት ይሆን?
ጥር 21, 2008

በይርጋ አበበ

ታዋቂውና ውጤታማው የዋልያዎቹ አጥቂ ሳላዲን ሰይድ በግብጽ እና አልጄሪያ የነበረውን የፕሮፌሽናል ፉት ቦል አቋርጦ በአሁኑ ሰዓት ክለብ አልባ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ በእረፍት ላይ ይገኛል። የተጫዋቹን አገልግሎት ለማግኘት የተለያዩ የግብጽ እና የሱዳን ክለቦች እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች እየዘገቡ ቢሆንም ተጫዋቹ ግን ሰሞኑን ከአንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከአንድ የግብጽ ክለብ ጋር እየተደራደረ መሆኑን ተናግሯል።

በሌላ በኩል የቀድሞ የተጫዋቹ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫዋቹ ማረፊያ ለመሆን በሩን ከፍቶ እየጠበቀው መሆኑን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም የገለጹ ሲሆን ተጫዋቹም በግሉ የውጭ አገር ክለብ ማግኘት ካልቻለ በፈረሰኞቹ ማሊያ ልናየው እንደምንችል ፍንጭ ሰጥቷል። ለመሆኑ የዋልያዎቹን እና የፈረሰኞቹን ውጤታማ አጥቂ በቀጣይ ከየትኛው ክለብ ጋር እናየው ይሆን?

በሌላ ዜና የአጥቂ ችግር ያለበት ኢትዮጵያ ቡና ከተለያዩ ተጫዋቾች ጋር ስሙ እየተያያዘ ይገኛል። አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አጥቂም በአሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች አማካኝነት የሙከራ ጊዜ ተሰጥቶት ከክለቡ ጋር ልምምድ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። ከቡና ጋር የሙከራ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን ተጫዋች አግኝተን በቅርቡ ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bikila [762 days ago.]
 ow my god salah,salah ,salah always I saying because salah is best footboler and have agood personal behavior

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!