የማይበገሩት አንበሶች እና ዋልያዎቹ በሱፐር ስፖርት እይታ
ጥር 13, 2008

በይርጋ አበበ

ሩዋንዳ አራተኛውን የቻን ዋንጫ ውድድር በሶስት ስታዲየሞቿ እያስተናገደች ሲሆን በውድድሩ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በመድረኩ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ትናንት በሁዬ ስታዲየም ከካሜሩን አቻው ጋር ተጫውቶ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ጎል ሳያስቆጥር ወጥቷል። ብሄራዊ ቡድኑ ትናንትም ጎል ሳያስቆጥር ይውጣ እንጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነጥብ ያገገኘበትን ውጤትም አስመዝግቧል። ይህንን ጨዋታ ተከታትሎ ጨዋታውን የተነተነው ሱፐር ስፖርት የሚባለው የእግር ኳስ ዘጋቢ ከዚህ በታች ያለውን ሀሳብ አስቀምጧል። እኛም ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አሰናድተነዋል።

የጎል ሙከራዎችን በተመለከተ

ሙሉዓለም ጥላሁን በብቸኝነት የተሰለፈበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኤሊያስ ማሞ እና ሙሉዓለም ጥላሁን አማካኝነት ሙከራ አድርገው ነበር። ነገር ግን የጎል ክልሉን ነቅቶ ይጠብቅ የነበረው የካሜሩኑ ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ሁጎ በቀላሉ ሊቆጣጠራቸው ችሏል። የካሜሩኑ አጥቂ ፍራንክ ቦያ ያደረገውን ሙከራም የሙገር ሲሚንቶው አቤል ማሞ በመዳፎቹ ቁጥጥር እንዳደረገው ይሄው የሱፐር ስፖርት ዘጋቢው አሸር ኮሙጊሻ አስፍሯል።

የጨዋታ ብልጫ እና አሰላለፍ

በርካቶች በቴሌቪዥን መስኮት እንደተከታተልነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካለፉት ጨዋታዎቹ በተሻለ በትናንትናው ጨዋታ ጥሩ የነበረ ሲሆን ለዚህ ደግሞ በተለይ የዳሽን ቢራው አማካይ አስራት መገርሳ ተወዳሽ ሆኗል። አስራት መገርሳ በዋልያዎቹ በኩል ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ የተመሰገነ ቢሆንም የጨዋታው ኮከብ ሆኖ የተመረጠው ግን የካሜሩኑ ያዚድ አቱባ ኤማኒ ነው ሲል አሸር ኮሙጊሻ ገልጿል።

የሱፐር ስፖርት ዘጋቢው በእለቱ በተለይ ካሜሩኖች ፍራንክ ቦያን በስቴፈን ጊንጉ ምፖንዶ ቀይረው ካስገቡ በኋላ በመሃል ሜዳው ላይ የጨዋታ እና የክሬቲቪቲ የበላይነቱን ካሜሩኖች እንደወሰዱ ይገልጻል። ዘገባው አያይዞም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የአርባምንጭ ከነማውን ታደለ መንገሻን በኢትዮጵያ ቡናው ኤሊያስ ማሞ ቀይረው ያስገቡ ሲሆን አጥቂውን ሙሉዓለም ጥላሁንን በታፈሰ ተስፋዬ የቀየሩበት ሰዓት የጨዋታው መገባደጃ አካባቢ ስለሆነ ውጤቱን ፈልገውታል ብሎ እንዲያስብ እንዳደረገው ይገልጻል።

በቻን ዋንጫ ምድብ ሁለትን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በስድስት ነጥብና አምስት የጎል ክፍያ አናት ላይ ሆኖ ሲመራ ካሜሩን በአራት ነጥብና አንድ የጎል ክፍያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ በአንድ ነጥብና ሶስት የጎል እዳ ተሸክሞ ምንም ነጥብ ያላስመዘገበውን አንጎላን በልጦ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ዋልያዎቹ ከምድባቸው ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ለማለፍ የምድባቸውን የመጨረሻ ጨዋታ ተጋጣሚያቸውን አንጎላን በሶስት ጎል ልዩነት ማሸነፍ የሚገባቸው ሲሆን በአንጻሩ የምድቡ መሪ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካሜሩንን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
mulatdesalegn [728 days ago.]
 bravo asrat megersa drom bihon yohannis kemeretachew lijoch anseh sayihon betesasatew ysahle lij policy miknyat newuna berta tenkir.ato yohannis ebakh ager yante melemameja ayidelemn lemiseru sewoch likeki botawun.

Yoni [728 days ago.]
 እዉነት ብሄራዊ ቡድን ነበሩ ! ያየ ይፈርዳል እንደሚመራ ቡድን ሰአት መግደሉ ምን ይሉታል ለመሆኑ አቻ ያሳልፈናል እንዴ ምኑ ደ*ብ አሰልጣኝ አጋጠመን በዛዉ .................................??????? ፌደረሽኑ ሆዳም አሰልጣኙ ሆዳም ለእግር ኳሱ መውደቅ ከ 2 ቱ ውጭ ተጠያቂ ማንም የለም ፈጣሪ አንድ ይበለን እንጅ ...!!!! እዉነት ለመናገር አቶ ሰዉነት ክብር ይገባቸዋል ምናለ ቢመለስ ጀግና ነዉ::

Sisay [727 days ago.]
 ቡድን እንኳን መስራት የማይችል አሰልጣኝ ቢኖር ዮሃንስ ነው፥፥ ከካሜሮን ጋር አቻ ወጥቶ እንዴት እንደተደሰተ እንዴ አቻ መውጣት እኮ አያሳልፈውም ቀድሞ ምን ሲል ነበር ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ነው የምንጫወተው ከባለፈው ቻን ቡድን የተሻለ ነገር ይዘን ለመመለስ ነው የምንሄደው ምናምንንንንንንንንንንን ባጣም ያሳፍራል ያሳዝናል ምን አይነት ኮች ነው ባካችሁ ሆሆሆሆሆሆሆ

tilk [727 days ago.]
 ምን አይነት አሰልጣኝ ነው። ቡድን መገንባት እማይችል።

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!