ዋልያዎቹ ከውጤት በስተጀርባ በማልያቸውም አወዛጋነታቸው እየታየ ነው
ጥር 15, 2008

የዋልያዎቹ ማሊያ ጉዳይ 

በ4ኛው ቻን ሩዋንዳ ላይ ከካሜሮን ጋር በተደረገው ጨዋታ ዋልያዎቹ ለብሰው የነበሩት ሙሉ ቢጫ ማልያ በለጠፈው ስም ምክንያት አጨቃጫቂ ነበር፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን ደንብ የተጣረሰ ነው በሚል በማሊያው ላይ ያለው ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ በነጭ እንዲሰረዝ ተደርጎ ነበር፡፡ ሰሞኑን የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በአውስትራሊያ የሚገኝ የትጥቅ አምራች ኩባንያ በAMS አማካኝነት ለቡድኑ አዲስ የማሊያ ዲዛይን እንደቀረበ ነው፡፡ የዋሊያዎቹ ቁልፍ ተጨዋች ጋቶች ፓኖም ለብሶት በሶሻል ሚዲያዎች ሊያስተዋውቀው ሞክሯል፡፡ ሶካአፍሪካ እንደዘገበው ይኸ ማልያ ማቲው ዎልፍ በተባለ ሰው የቀረበ ዲዛይን ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሊያው ከስፖርት ቤተሰቡ ተቀባይነት እንደማያገኝ በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ ዋናው ምክንያት ደግሞ አረንጓዴና በበቂ ሁኔታ መደብ ቀለማት ባለመሆናቸው ነው፡፡
Walia Jersey


 የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ስልጣኑን ከተረከበ ወዲህ በማሊያው ላይ ምንም አይነት ቋሚ ውሳኔ ያሳለፈ አይመስልም፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ከሜዳ ውጪና በሜዳ ላይ ቡድኑ የሚያደርገው ማሊያ የተዘበራረቀ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ታዋቂውን ባለሸንተረር ማሊያ ሌላ ጊዜ ሙሉ ቢጫ አንዳንዴ ደግሞ አረንጓዴ ማሊያ እያደረገ የአገርን ክብር እያዘበራረቀ ነው፡፡ ይባስ ብሎ በቻን ውድድር ላይ በብሄራዊ ቡድኑ ማሊያ ላይ የተወሰነው ሁኔታ የፌዴሬሽኑን ትኩረት አለመስጠት ያመለክታል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በ2014 እ.ኤ.አ የተመሰረተው የአውስትራሊያ ኩባንያ ያቀረበው የአዲስ ማሊያ ፕሮፖዛል ሙሉ ቡኒ ቀለም የበዛበትና ባህላዊ ሁኔታዎች የሚንፀባረቁበት ነው፡፡ ማሊያው ቢጫና አረንጓዴ ቀለሞችን ደንቡ እንደሚያስገድደው መደበኛ ቀለማት ስላልሆኑበት የሚያሳስብ ነው፡፡ በኤኤምኤስ የቀረበው የማሊያ ዲዛይን ተቀባይነት አገኘም፤ አላገኘም በብሔራዊ ቡድኑ ማሊያ ቋሚነት፤ ልዩ መለያና ቀለም ዘላቂ ውሳኔዎች እንደሚያስፈልጉ አስተያየቶች እየተሰጡ ናቸው፡፡ የአውስትራሊያው ኩባንያ ኤኤምኤስ ለደቡብ ሱዳን፣ ለሩዋንዳና ለሴራሊዮን ባለፉት ሁለት ዓመታት የብሔራዊ ቡድኖቻቸውን ማሊያ በማቅረብ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከቻን ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሊያ አሰርቶ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ከሁለት እና ከሦስት አመታት በፊት በአፍሪካ ዋንጫና በቻን ውድድር ታዋቂ የሆነው ባለሸንተረሩ ማሊያ ከዋሊያዎቹ ባሻገር በስፖርት ቤተሰቡ ያገኘው ተቀባይነት ከግምት ውስጥ ገብቶ ለቡድኑ ቋሚ ማልያ መወሰን አለበት፡፡ ባለሸንተረሩ ማሊያ ከሦስት ዓመት በፊት ከዋሊያዎቹ ስኬት ጋር በተያያዘ በቀን እስከ 250 በነጠላ ይቸበቸብ የነበረ ሲሆን ዋጋቸውም እንደየጥራት ደረጃው ከ50-200 ብር ይሸጥ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የተለያዩ አስመጪና ላኪ ኩባንያዎችም ከቻይና እስከ 10,000 ማሊያዎችን በማስመጣት እየነገዱ ነበር፡፡ ምናልባትም ይህ ሁኔታ ከዋልያዎቹ ስኬት ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ራሱ በ75 ብር ከ15,000 ማልያዎችን ለገበያ በማቅረብ የተጠቀመበት ሁኔታም አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ከቻን መልስ የብሔራዊ ቡድኑ ማልያ ጉዳይ እልባት ማግኘት ይጠበቅበታል፡፡

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gizegeta [760 days ago.]
 ሃገር ወዳድ መሪዎች የሌሏት ብቸኛ ሃገር ብትኖር የኛዋ ኢትዮጵያ ናት ባንዲራ ክብር የሌለባት ሃገር ብሔራዊ ቡድኑን ሲፈልጉ ነጭ ማሊያ ሲፈልጉ ቀይ ያሻቸውን እያለበሱት ባንዲራ አልባ ካስመሰሉን ቆየን እኮ ጎበዝ !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!