የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን የሚኖረውን ቆይታ የሚወስንበት ጨዋታ
ጥር 16, 2008

በይርጋ አበበ

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘውና ሩዋነዳ እና አይቮሪኮስት ከምድብ አንድ ተከታትለው ወደ ሩብ ፍጻሜ ባለፉበት አራተኛው የቻን ዋንጫ የምድብ ሁለት ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ከአመሻሹ 11 ሰዓት ላይ ይካሄዳሉ። ሁለቱም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት የሚካሄዱ ሲሆን የምድቡ መሪ እና ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፏን ቀድማ ያረጋገጠችው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተከታይዋ ካሜሩን እንዲሁም የምድቡ ግርጌዎቹ ኢትዮጵያ ከአንጎላ ጋር ይገናኛሉ። በዚህ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከአንጎላ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በሁለት ጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻሉ እና በተመሳሳዩ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ካሜሩንን በሁለት ጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻለች ዋልያዎቹ ወደ ሩብ ፍጻሜ በማለፍ ታሪክ ይሰራሉ ማለት ነው።

ዋልያዎቹ አንጎላን በሰፊ የጎል ልዩነት ቢያሸንፉ እንኳ የካሜሩን መሸነፍ የማይጠበቅ ሊያደርገው ይችላል። ለዘሀ ደግሞ ምክንያቱ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከምድቧ ማለፏን ቀድማ ያረጋገጠች በመሆኑ በዛሬው ጨዋታ ቋሚ እና ወሳኝ ተጫዋቾቿን ላትጠቀም ትችላለች ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ማለት ትናንት በምድብ አንድ ከሞሮኮ ጋር የተጫወተችው አስተናጋጇ ሩዋንዳ በሞሮኮ አራት ለአንድ የተሸነፈችበትን ጨዋታ እንደ አስረጂ ምክንያት ማንሳት ይቻላልና ነው።

በሌላ በኩል የዋልያዎቹ አማካይ ተከላካይ ጋቶችፓኖም በሁለት ተከታታይ የልምምድ ፕሮግራሞች ላይ እንዳልተገኘ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ይህም ተጫዋቹ ጉዳት ሳይደርስበት እንዳልቀረ ይገመታል። በዚህም የተነሳ በዛሬው ጨዋታ ጋቶች ፓኖም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ብሔራዊ በቡድንን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ ከአሰላለፍ ውጭ የሚሆንበት አጋጣሚ ይሆናል ማለት ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
yilkal [690 days ago.]
 This is the time to think again. Two years ago EFF sack Coach Sewnet Bishaw. After the removal of Sewnet Ethiopian soccer standard decline. I advice you EFF do not be ridged, give two years time to Swenet Bishaw agin.

Daniman [690 days ago.]
 "ተከብረሽ የኖርሽው በነ ‪#‎አዳነ‬-ግርማ ይጫወትብሻል የማንም ገገማ …" "ተከብረሽ የኖርሽው ‪#‎በሰውነት‬-ቢሻው ዩሀንስ መጣ ና አረገሽ እንዳሻው…"

Samuel Bezabeh [689 days ago.]
 እኔ በጣም የገረመኝ የአሰልጣኙ (ዮሀንስ ሳህሌ) የወረደ የአሰልጣኝነት ብቃት ነው፡፡ እኔ ፌዴሬሽኑ ምን እየሰራ እንደሆነ ነው እቆቅልሽ እየሆነብኝ ያለው፡፡ ደግሞ ቃለመጠይቅ ሲደረግለት በውጤቱ ረክቻለሁ በማለት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያላግጣል ፌዴሬሽኑ ይህንን አሰልጣኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማባር ነው ያለበት፡፡ የኳስ እውቀት የሌለው መሀይም አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ፡

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!