ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ካሜሩናዊያን አጥቂዎችን አስፈረመ
ጥር 16, 2008

በይርጋ አበበ

የአጥቂ ችግር እንዳለበት በተደጋጋሚ ሲናገር የቆየው ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፕሪሚየር ሊጉ በተቋረጠበት በዚህ ወቅት ሁለት ካሜሩናዊያን ተጫዋቾችን ማስፈረሙን የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም በሰጡት የስልክ ቃለ ምልልስ አስታወቁ።

የዓለም አቀፍ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በተከፈተበት በዚህ ወቅት ቡድናቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ተቆዩት አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ሁለቱን ካሜሩናዊያን አጥቂዎች በሰጧቸው የሙከራ ጊዜ ለክለባቸው ብቁ መሆናቸውን ስላረጋገጡ ሊያስፈርሟቸው ችለዋል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተቋረጠበት ሲመለስና ውድድሩ መካሄድ ሲጀምር ሁለቱም አጠቂዎች ለክለባቸው ጨዋታ እንደሚያካሂዱ ከፌዴሬሽኑ ይሁንታ ተሰጥቷቸዋል።

ተጫዋቾቹ በኢትዮጵያ የሚያሰራቸውን የስራ ፈቃድ ማግኘት ከቻሉ በቀጥታ ወደ ጨዋታ እነደሚገቡ የሚታወቅ ሲሆን ተጫዋቾቹ ቀደም ሲል ይጫወቱ የነበሩት ፓትሪክ የሚባለው ለላሜሩኑ ድራጋን ክለብ ያውንዴ እና ኒዳኒ የሚባለው ደግሞ ለሊባኖሱ ሻባብ አል ጋህዚ እንደነበረ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና ክለቡ ከየመኑ አልሳክር ክለብ ኢትዮጵያዊ አማካይ ተጫዋች ማስፈረሙን አስታወቀ። ተጫዋቹ ኤሚያስ በለጠ የሚባል ሲሆን ለቡና ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት የፈረመ ሲሆን ወርሃዊ ደመወዙም 15 ሺህ ብር መሆኑ ታውቋል። የየመኑ አልሳክር ክለብ ቀደም ሲል አንዋር ሲራጅ ይጫወትበት የነበረ ክለብ መሆኑ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ቡና ነገ ከቀኑ 8፡30 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፎ .እንደሚጫወት ተገልጿል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!