ሉሲዎቹ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተመለሱ
ጥር 23, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ከሆኑ በኋላ በድጋሚ ወደ ማጣሪያው መመለሳቸውን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ። የካፍን ውሳኔ ጠቅሶ ለዝግጅት ክፍላችን መረጃወን ያደረሰን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ሉሲዎቹ ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር ያካሂዳሉ ለዚህ ጨዋታም በቅርቡ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ ብሏል።

 

ሉሲዎቹ ከማጣሪያ ውጭ ከሆኑበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በድጋሚ እንዲመለሱ የተደረገው የቶጎ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ከውድድሩ ማግለሉን ተከትሎ ነው። የሉሲዎቹ እና የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታም እ.ኤ.አ ከማርች 4 እስከ 20 ባሉት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአልጄርስ አካሂደው የመልሱን አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ የፌዴሬሽኑ መግለጫ አስታውቋል።

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከምዝገባ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ክፍተት እንደነበረ የገለጸው የፌዴሬሽኑ መግለጫ ነገር ግን በተለይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በካፍ ዋና ጽ/ቤት ካይሮ እና የቻን ውድድር በተካሄደበት ሩዋንዳ ተገኝተው ከካፍ አመራሮች ጋር ባደረጉት ያለሰለሰ ውይይት መሳካቱን አስታውቋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!