ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነቱ ሲመለስ ደደቢት አቻ ወጣ ፈረሰኞቹ የሊጉን መሪነት ተረከቡ
ጥር 25, 2008

በይርጋ አበበ

ከአንድ ወር መቋረጥ በኋላ ትናንት ሰኞ በድጋሚ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስት ጨዋታዎች ተካሂደውበታል። ሊጉ ትናንስ ሰኞ በጀመረበት እለት ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለቱን የደቡብ ክልል ክለቦች ሆሳዕና ሀድያን እና ሀዋሳ ከነማን በአን ጎል ልዩነት ማሸነፍ ችለዋል።

የአሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማሪያም ንግድ ባንክ በቀኝ መስመር ተከላካዩ አንተነህ ገብረ ክርስቶስ አስቆጥሯል። ኤሌክትሪክ በበኩሉ በተከላካዩ ሲሴ ሃሰን እና አሳልፈው መኮንን ሁለት ጎሎች ቀድሞ በታፈሰ ሰለሞን አማካኝነት ጎል አስቆጥሮ መምራት የቻለውን ሀዋሳ ከነማን ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ችሏል። የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ክለብ ሀዋሳ ከነማ አዲስ ካደገው ሆሳዕና ሀድያ ጋር የሊጉን ግርጌ በብቸኝነት ተቆጣጥረውታል።

ዛሬ አመሻሹ ላይ ከተካሄዱት ሶስት ጨዋታዎች መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደው ደደቢት አንድ እኩል ተለያይቷል። ደደቢት በሳሙኤል ሳኑሜ ጎል አርባ ምንጭ ደግሞ በተሾመ ታደሰ ጎል ነው ነጥብ ተጋርተው የወጡት።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ አስር ሰዓት የጎንደሩን ዳሽን ቢራን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል። ሁለቱን አምበሎቹን መስዑድ መሃመድን እና ጋቶች ፓኖምን ያላሰለፈው ኢትዮጵያ ቡና በኤሊያስ ማሞ አምበልነት እየተመራ ጨዋታውን የጀመረ ሲሆን በዳሽን ቢራ ላይ የተጎናጸፈውን ድል ያገኘውም በኤሊያስ ማሞ እና ያቡን ዊሊያም ጎሎች ነው። ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 11 ማድረስ የቻለ ሲሆን ደረጃውንም ወደ አራት አሳድጓል።

ከአመሻሹ 11፡30 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ በበኩላቸው በአዳነ ግርማ ሁለት ጎሎች እና በብሪያን አሙኒ አንድ ጎል ሶስት ለባዶ አሸንፈው ሙሉ ሶስት ነጥብ በማግኘት የሊጉን መሪነት ከአዳማ ከነማ ላይ መቆጣጠር ችለዋል። አዳነ ግርማ በ49ኛው እና በ70ኛው ደቂቃ ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን የመጀመሪያዋን ጎል ያስቆጠረው በመለያ ምት ነው። አዳነ ዛሬ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ክለቡን ብቻ ሳይሆን ራሱንም በግሉ የሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት ከአዳማ ከነማው ታፈሰ ተስፋዬ ላይ መውሰድ ችሏል።

ሊጉ ነገም ቀሎ ውሎ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ አዳማ ከነማ በሜዳው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲዳማ ቡናን ሲያስተናግድ መከላከያ ድሬዳዋ ከነማን 11፡30 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገጥማል።    

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Babi [715 days ago.]
 Adane Girma will win top scorer of this year ! Gooooooooooo Aduuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuu !

bikila [715 days ago.]
 aye bunye eshit eshit new yalut sanjawoch eski wedemerinet bik belu nafeken eko estadom memitat. min kereh atilum selamawi fugera lemesmat. tiz yilachihual bemekelakeya sitshenefu dfaf truck min endaluachihu bunann eshit esahit sike ebete gebahu. enam befeterachihu wede lay tega beluna dimketum yiketil enem wede cambolojo limita.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!