ኢትዮጵያ ቡና እና ሀበሻ ቢራ ለተጨማሪ ዓመታት አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ
ጥር 26, 2008


ላፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ኢትዮጵያ ቡናን በማሊያ ስፖንሰር በመሆኑ የሚታወቀውና በቅርቡ ወደ ገበያ የገባው ሀበሻ ቢራ ከቡና ጋር ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት አብሮ ለመስራት መስማማቱን የኢትፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ገለጹ። ክለቡ እና ቢራ ፋብሪካው ስምምነት ላይ የደረሱት በዓመት 12 ሚሊዮን ብር ለመክፈል ሲሆን ክለቡም በዋናነት የክለቡ ማሊያ ፊት ክፍል መሃል ላይ የቢራ ፋብሪካውን ማሳታዎቂያ ይለጥፋል።

ምርት ከመጀመሩ በፊት ከቡና ጋር አብሮ በመስራት ውጤታማ መሆኑን ቀደም ብሎ የገለጸው ቢራ ፋብሪካው በዚህ የውድድር ዓመት ክለቡን እያሰለጠኑ ያሉትን ድራጋን ፖፓዲች ሙሉ ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ሲሸፍን መቆየቱን ቀደም ሲል የክለቡ የቦርድ አመራሮች ገልጸው ነበር። የሁለቱን ወገኖች የስፖነሰር ሺፕ ስምምነት ዝርዝር መረጃ እንዳገኘን እንመለሳለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!