በዘጠንኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አምስቱን የአዲስ አበባ ክለቦች ወደ ደቡብ ክልል ይወስዳል ፤ ደደቢት ወደ ጎንደር ያቀናል
ጥር 27, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠንኛ ሳምንት ነገ እና እሁድ በሚካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል። የሊጉ ሁሉም ጨዋታዎች በክልል ከተሞች የሚካሄዱ ሲሆን ባሳለፍነው ማክሰኞ ወላይታ ድቻን ሶስት ለባዶ ማሸነፍ የቻሉት የሊጉ ሻምፒዮኖች ፈረሰኞቹ በዘጠንኛው ሳምንት ደግሞ ሌላኛውን የደቡብ ክልል ክለብ ለመግጠም ወደ አርባምንጭ ያመራሉ። ዳሽን ቢራን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት ለባዶ ያሸነፉት ቡናማዎቹ ደግሞ ወደ ሀዋሳ አቅንተው በውጤት ቀውስ ውስጥ ያለውን ሀዋሳ ከነማን ይገጥማሉ። ሁለቱም ጨዋታዎች እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይካሄዳሉ።

ደደቢት ወደ ጎነደር ተጉዞ ከዳሽን ቢራ ጋር ሲጫወት ኤሌክትሪክ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ከሲዳማ ቡና ጋር ይጋጠማል። መከላከያ ወደ ሆሳዕና ተጉዞ ከሊጉ ግርጌ ሆሳዕና ሀድያ ጋር የሚጫወት ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ቦዲቲ ተጉዞ  ወላይታ ድቻን ይገጥማል። የሊጉ መሪ አዳማ ከነማ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ተጉዞ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር የሚያደርገው ጨዋታም ተጠባቂ ነው።

ሁሉም ጨዋታዎች ከአዲስ አበባ ውጭ መካሄዳቸውን ተከትሎ ጨዋታዎቹ በሙሉ በተመሳሳይ ሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የሚካሄዱ ይሆናል። ሊጉን አዳማ ከነማ በ20 ነጥብ ሲመራ ፈረሰኞቹ በ19 ይከተላሉ። ሆሳዕና ሀድያ እና ሀዋሳ ከነማ ደግሞ የታችኛውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘውታል። ታፈሰ ተስፋዬ በሳት ጎሎች የሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት ሲመራ የፈረሰኞቹ ምክትል አምበል አዳነ ግርማ ደግሞ በአንድ ጎል ተበልጦ ይከተለዋል።

ድሬዳዋ ከአዳማ ፣ ሲዳማ ከኤሌትሪክ ፣ ወላይታ ከንግድ ባንክ  የሚያደጉት ጨዋታ ሰኞ በተመሳሳይ 9ኝ ሰአት የሚካሄድ ሲሆን ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ግን እሁድ በተመሳሳይ 9ኝ ሰአት ላይ ይካሄዳሉ።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Bereket (Beka) [711 days ago.]
 @ Bubu ዝም ብለህ የመንደር የሴት እድር ወሬ አታውራ የሰው ስም ጠርተህ ከህግም አኳያ ያስጠይቅሃል:: ጉቦ ሲሲጥ ያየህ አትመስልም .... አሁን አፍህን ከፍተህ ስትናገር ! ለቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰጠውም ፔናሊቲ ተገቢ ነው ምክንያቱም የደጉ ደበበ ማሊያ በመጎተቱ :: ጥላቻ ጭፍንነት ጥሩ አይደለም ይልቅ በወሬ ስም ከምታጠፉ ስራ ሰርታችሁ ተፎካከሩ :: ጊዮርጊስ ማሸነፍ ያንሰዋል ለዛውም ብዙ ኳሶች የግቡ አግዳሚ መልሷቸው ነው :: ስራ ... ስራ... ስሩ ወሬ አይነፋም !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!