ዋልያዎቹ ወደ ታች የሚያደርጉትን ጉዞ አላቆሙም
ጥር 27, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ወርሃዊ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ ከነበሩበት 118ኛ ወደ 124ኛ ወርደዋል። ከአፍሪካ ደግሞ 33ኛ ላይ ተቀምጠዋል። ጀርመን የዓለምንና የአውሮፓን አልጄሪያ ደግሞ የአፍሪካን እግር ኳስ በሚመሩበት በፊፋ ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሚሰለጥኑት ዋልያዎቹ ካለፉት ስምንት ወራት ወዲህ በየጊዜው ደረጃቸው እየወረደ ሄዷል።

ለመሆኑ ዋልያዎቹ ለምን ደረጃቸው እየወረደ ሄደ? ለሚለው ጥያቄ ቀደም ሲል ከጋዜጠኘች ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ “ቡድኑን ከተረከብኩበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ጨዋታዎችነ በማሸነፍ ላይ ብንሆንም ደረጃችን ግን መሻሻል አላሳየም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በፊፋ ካላንደር የሚመራ የወዳጅነት ጨዋታ አለማካሄዳችን እና የገጠምናቸውና ያሸነፍናቸው ቡድኖች ደረጃ ከፍተኛ ባለመሆኑ ነው” ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፊፋ የአገራትን ደረጃ ሲያወጣ መመዘኛ ከሚያደርጋቸው መካከል አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የተናገሩት አንዱ ሲሆን በተገባደደው የጃንዋሪ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ እውቅና ያለው ጨዋታ አላካሄደም። ከፊፋ እውቅና ውጭ አራት ጨዋታዎችን ያካሄደ ሲሆን ከአራቱ በሁለቱ ተሸንፎ በሁለቱ ደግሞ አቻ መውጣት ችሎ ነበር።

የዋልያዎቹን የቁልቁለት ጉዞ በተመለከተ አንባቢያንም ሀሳባቸውን እንዲያፍሉ እንጋብዛለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
JustThinkin [680 days ago.]
 In few weeks time, the EPL will be suspended to prepare for the two Algeria games. There hasnt been a firstteam match at senior level friendly or otherwise for monthes. And as usual, few days from the next match, everyone will be asking if there will be any friendly game to assess the preparedness of the players. Instead, the EFF should be looking at its budget and start enquiring for countries who are interested to play a friendly. Those who are willing to pay for thier own expenses are welcome. Can EthioFB find out what the EFF are planning for the next crucial games against Algeria home and away.

JustThinkin [680 days ago.]
 Dear EF, Where did you get the stats for Germany and Algeria from? Please doublecheck info before publishing misleading info. Thanks

የኢትዮጵያ ፉትቦል ፌዴሬሽን [679 days ago.]
 የሚያስገርም ነበር ከዚ ቀደም የሰሩት እንዳልሰሩ አድርጎ ኮንኖ ቦታዉን ስትረከቡ ግን እናነተን እንደማይመለከት ሇናችሁ ነው ያየናችሁ ለመሆኑ የኢ ፉ ፌ አመራሮች አላችሁ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሐገር ከቶናል አለን ካለችሁ የቀጠራችሁት አሰልጣኝ የሀገሪቱ ን ፉትቦል ቁልቁል ሲሰደው ባላያችሁ ነበር ስራችሁ ከህዝቡ አልፎ ለራሳችሁም አሳፍሯችሁ ከቴሌቭዥን መስኮትም አስጠፋችሁ ይልቅስ ቀርባችሁ ስሩ ህዝባችሁን ይቅርታ ጠይቁ እጅግ አድምታችሁታል የናተ ጉድ ቢወራ አያልቅም ለማንኛውም ስራ ሰርታች ሁ ለመገናኘት ያብቃን

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!