ዛሬ ስለሚካሄዱ አራት ጨዋታዎች አንዳነድ ነጥቦች
ጥር 29, 2008


በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከበርካታ አስገራሚ እና አወዛጋቢ ገጠመኞቹ መካከል ተጫዋቾችና እና አሰልጣኞች በአንድ ክለብ ተረጋግተው የሚቆዩ ባለመሆናቸው ዘንድሮ አንዱን ክለብ ያስጨፈረ አሰልጣኝ ወይም ተጫዋች በቀጣዩ ዓመት ያምናውን ክለቡን አንገት ሲያስደፋ መታዩ ይጠቀሳል። በየምክንያቱ መቆራረጡ ደግሞ ሌላው አስገራሚ ክስተቱ ነው። ለ40 ቀናት ተቋርጦ የቆየው ሊግም ባሳለፍነው ሰኞ እና ማክሰኞ እንደገና መካሄድ ሲጀምር የሊጉ ታላላቅ ክለቦች ድል ሲቀናቸው መሪው አዳማ ከነማ በሜዳው ከሲዳማ ቡና ጋር ነጥብ ጥሎ ነበር።

ዛሬ የሊጉ ዘጠንኛ ሳምንት መርሃ ግብር በአራት የክልል ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል። ሊጉ በዚህ ሳምንት አንድም ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ የማይካሄድ መሆኑ ክስተቱን አስገራሚ የሚያደርገው ሲሆን ሌላው አስገራሚ ገጠመኝ ደግሞ ከስድስቱ የአዲስ አበባ ክለቦች መካከል አምስቱ ወደ ደቡብ ክልል ማምራታቸው ነው። ወደ ደቡብ ክልል ያላቀናው ብቸኛው አዲስ አበባ ላይ መቀመጫውን ያደረገው ክለብ ደደቢት ነው። ደደቢት ወደ ጎንደር ተጉዞ ከዳሽን ቢራ ጋር የሚጫወት ይሆናል። ዛሬ የሚካሄዱትን አራት ጨዋታዎች ከዚህ በታች ተመልክተናቸዋል።

አርባ ምንጭ ከነማ ከፈረሰኞቹ

አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጠንካራ ትስስር አላቻው። ከቅርብ ዓመታቱ ግጥምጥሞሽ እንኳ ብንጀምር ፈረሰኞቹ በ1990 ዓ.ም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድጉ የቡድኑ ኮከብ ጎል አግቢ የነበረው ስንታየሁ ጌታቸው ወይመ ቆጬን ያገኙት ከአርባ ምንጭ ከተማ ነው። በ1995 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ እና ክስተት ክለብ የነበረው አርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ በመጨረሻው ሳምንት ዋንጫውን በፈረሰኞቹ ሲነጠቅ ኮከብ ተጫዋቹን ደጉ ደበበንም ለፈረሰኞቹ አሳልፎ ሰጥቷል። አሁን በአርባ ምንጭ ከነማ እየተጫወተ የሚገኘውን ታደለ መንገሻን እና አሁን የፈረሰኞቹን የግራ መስመር ተከላካይ አበባው ቡታቆን ፈረሰኞቹ በተቀራራቢ ዓመታት ከአርባ ምንጭ ከተማ ማህጸን ተቀብለው ያሳደጉ መሆናቸው ይታወሳል። 

ከተጫዋቾች ዝውውር በዘለለ ደግሞ ፈረሰኞቹ በአርባ ምንጭ ከተማ ተወካዮቹ ላይ የነጥብ የበላይነት ያላቸው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከነማ የተሸነፉት የዛሬ ዓመት ነበር። አርባ ምንጭ ላይ የተካሄደውን ጨዋታ ባለሜዳዎቹ አንድ ለባዶ አሸንፈው የወጡ ሲሆን በመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሶስት ለባዶ ፈረሰኞቹ ማሸነፍ ችለዋል።

ሀዋሳ ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና

በአሁኑ የሀዋሳ ከነማ ቡድን ውስጥ ሁለት የቀድሞ የቡና ተወዳጅ ሰዎች ይገኛሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቡና ደጋፊዎች በእጅጉ ይወደድ የነበረው አስቻለው ግርማ እና የቡና የምንጊዜም ተወዳጅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ። ባለፈው ዓመት ሁለቱ ክለቦች ሶስት ጊዜ እርስ በእርስ ተገናኝተው የሀዋሳ የበላይነት ታይቶበት ነበር የተጠናቀቀው። ሁለት ጊዜ ሀዋሳ ከነማ ሲያሸንፈ አንዱን ደግሞ በአቻ ውጤት ነበር የተለያዩት።

ስምንተኛ ሳምንት የሊጉን ጨዋታቸውን ያጠናቀቁት ቡና በዳሽን ቢራ ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ሲሆን ሀዋሳ ደግሞ በኤሌክትሪክ ሁለት ለአንድ ተሸንፎ ነበር። በአሁኑ ወቅት በሊጉ ሀዋሳ ከነማ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቡና ደግሞ 11 ነጥቦችን የዞ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዛሬው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንደሚጫወቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ሀዋሳ ከነማ ከአምበሉ ሙሉጌታ ምህረት እና ሀይማኖት ወርቁ በጉዳት ከሜዳ መራቃቸው ቡድኑን እንደጎዱት ሜዳ ላይ ታይቷል። ቡናዎች አህመድ ረሺድን በጉዳት እንደማያሰልፉ የተረጋገጠ ሲሆን ጋቶች ፓኖም እና ግብ ጠባቂው ሀሪሰን የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

ዳሽን ከደደቢት

ዳሽን ቢራ አጀማመሩ ጥሩ ሆኖ ወደ መሃል እየተንሸራተተ የመጣ ክለብ ሲሆን ደደቢት በኩሉ ይህ ነው የሚባል ወጥ አቋም ማሳየት ሳይችል የቀጠለ ክለብ ነው። ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታውን በበላይነት ለማጠናቀቅ እምነታቸውን የጣሉባቸው ተጫዋቾች ሲኖሩ ዳሽኖች በግብ ጠባቂያቸው ቢኒያም ደደቢቶች ደግሞ በአጥቂያቸው ሳሙኤል ሳኑሜ ላይ እምነታቸውን ይጥላሉ። ዳሽን ቢራ ሲቀመጥ ደደቢት በአስር ነጥብ ዘጠንኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ 12 ነጥቦችን ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሆሳዕና ሀድያ ከመከላከያ

11 ነጥቦችን ይዞ በጎል ክፍያ ኢትዮጵያ ቡና በልጦ አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ተወዳዳሪው መከላከያ ባሳለፍነው ሳምንት ድሬዳዋ ከነማን ሁለት ለባዶ አሸንፎ ወደ ሆሳዕና ያቀና ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሌላውን አዲሱን የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ሆሳዕና ሀድያን ይገጥማል። ሆሳዕና ሀድያ አምስት ነጥቦችን ብቻ ይዞ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዛሬው ጨዋታም የአሸናፊነቱን ቅድሚያ ግምት ጦሩ ይወስዳል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ሽማሙ [677 days ago.]
  በጣም ደስ ብሎኛል ሃዋሳ ከነማ በማሸነፉ ብዙ ኳሶች ስተናል እንጂ ከ 1 ጎል የበለጠ አስቆጥረን ማሸነፍ እንችል ነበር የቡና ደጋፊዎች ግን ስርዓት የሚባል ነገር አያውቁም ጎሉ ልክ ሲቆጠርባቸው ድንጋይ መወርወር ጀመሩ ለነገሩ ገና ጨዋታው ሳይጀመርም ሲሳደቡና ሲዛለፉ ነበር

bikila [674 days ago.]
 min ayinet neger new yemitasayun erebakachiyhu hig yelem bageru,zare kenu sint new yemitilekulin zena yemeche new sint technology betyesatefebet alem yewere kuantama atasayun.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!