ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫዋቾችን ማበረታቻ ሽልማት አሳደገ
የካቲት 02, 2008


በይርጋ አበበ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ዋናው የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በየጨዋታው ለሚያስመዘግበው ውጤት የሚያበረክተውን የማበረታቻ ሽልማት ወይም ኢንሴንቲቭ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ አሽኔ ለዝግጅት ክፍላችነ በላኩልን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ክለቡ ውሳኔውን ያስተላለፈው ባሳለፍነው ማክሰኞ ለተጫዋቾች ዓመታዊ የተጫዋቾች ሽልማት በተበረከተበት እለት ነው። የኢንሴንቲቭ ሽልማቱን አስመልከቶ የክለቡ ዋና የቡድን መሪ አቶ ታፈሰ በቀለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ በፊት ለተጨዋቾች ይሰጥ የነበረው የጨዋታ ማበረታቻ 700 ብር እንደነበር ገልፀው ከዚያም በኋላ 300 ብር ጭማሪ በማድረግ ለተጨዋቾች የሚሰጠው የጨዋታ ማበረታቻ ገንዘብ ብር 1000 መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ የተጨዋቾች ኢንሴንቲቭ 1000 ከተደረገ በኋላ ምንም አይነት ጭማሪ ሳይደረግ ረዘም ያለ ጊዜ መቆየቱን በማስታወስ የስራ አመራር ቦርዱ ተጨዋቾቻችንን የበለጠ ሊያተጋ የሚችለው ኢንሴንቲቭ ምን ያህል ነው ? ተጨዋቾቻችን የክለቡን ባህልና እሴት በሜዳ ላይ ይዘው እንዲቀጥሉ የሚያደርገው ኢንሴንቲቭ ምንያህል ቢሆን ነው የሚሉት ሃሳቦች ላይ በመወያየት ቦርዱ ተጨዋቾችን ያነቃቃል፤ ለበለጠ ድል ያዘጋጃል ያለውን የጨዋታ ማበረታቻ ገንዘብ ከብር 1000 ወደ 1500 ብር ማደጉንና ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ዲቻ ከሚያደርጉት ጨዋታ ጀምሮ እንደሚታሰብ ተናግረዋል” ሲል የህዝ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ ጠቁመኟል።

መግለጫው አያይዞም የስፖርት ማህበሩ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ደንበል ባልቻ በስፍራው ተገኝተው “ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሌም ሻምፒዮን መሆን የሚፈልግ ክለብ ነው፡፡ስለዚህም በዘንድሮው አመትም ሻምፒዮን እንድንሆን እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህም ሁሉንም ጨዋታ በሜዳዬ እና ከሜዳዬ ውጭ ነው የምጫወተው ብላችሁ ሳትለዩ እኩል ክብደት ሰጥታችሁ እንድትጫወቱ ይህንን የማበረታቻ ሽልማት ጭማሪ አድርገናል፡፡ አመቱ ሲጠናቀቅም ከእናንተ ሻምፒዮንነትን እንጠብቃለን ብለዋል” ብለዋል ሲል ያስታወቀ ሲሆን “የዋናው ቡድን አምበል ደጉ ደበበ በበኩሉ እየተሰራ ማግኘት ማለት ይሄ ነው። ጨዋታ ማበረታቻ ክፍያው ከፍ መደረጉ የተጨዋቾችን የማሸነፍ መንፈስ የበለጠ ከፍ እንደሚያደርገው ገልጿል” በማለት አስታውቋል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ታፈሰ ሄሮ [744 days ago.]
 አሁን እሄ ቡድን ዋንጫ የምበለዉ በርግጥ እናንተስ የድሮ ጨርቃጨርቅን ለመበቀል ነበረ ግን አይሳካላቹ አያቹ እኛ አርባ ምንጮች ወኔ አለን ለማንም አንበገርም አሁንም እድሜ ለደቡብ ልጆች አኮራቹ ግን ከ አአ ብሆን ዋንጣ ቀርቆ የሱን ከለሩን አታዩም ነበረ ደሞ እናንተ ጋዝጦኞች ሰለ አም ስታወሩ አላርጅካቹ ይነሳባችዋል እንደ እናንታአጣቃላይ የደቡብናየአርባ ምንጭ ዉድቀት ለማየት ትፈልጋላቹ ግን ፈጣራችን መሬቷን ህዝቦቻን ባርኮ ሰቶላታል እና በመጨረሻ ልንገራቹ እሄ የናታ ገንዘብ ቀስን እንጅ ወነን አይገዛም ድል ለደቡብ ክለቦች።

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!