የዋልያዎቹና የፈረሰኞቹ የኋላ ደጀን ህክምናውን በጀርመን ሲከታተል ቆይቶ ተመለሰ
የካቲት 01, 2008በይርጋ አበበ

የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን ተከላካይ ሳላዲን ባርጌቾ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት በደረሰበት ጉዳት ለረጅም ጊዜ በጀርመን አገር ህክምናውን ሲከታተክ ቆይቶ መመለሱን ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስታወቀ። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የህዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን መግለጫ እንዳስታወቀው “ሳልሀዲን በርጌቾ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ሲያደርግ የጉልበት ጉዳት አጋጥሞት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ጉዳቱን ተከትሎም ሰልሃዲን በርጌቾ በሀገር ውስጥ በዕውቅ ስፔሻሊስቶች ሲሰጠው የቆየው ህክምና ለውጥ ባለማሳየቱ ለህክምና ወደ ጀርመን ሀገር መሄዱን በምንጊዜም ጊዮርጊስ የራድዮ ፕሮግራም ማሳወቃችን ይታወሳል” ሲል አስታውቋል።

 ሰልሃዲን በጀርመን ሀገር ለአንድ ሳምንት ባደረገው ህክምናም በጉልበቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ማሳየቱንና ቀሪውን ህክምናውንም በሀገር ውስጥ በሚገኙ የዘርፉ ስፔሻሊስቶች ጋር ቢከታተል ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ ጨዋታ መመለስ እንደሚችል ሀኪሞቹ ነግረውታል፡፡ « በጀርመን ሀገር የተሰጠኝ ህክምና በቪዲዮ የታገዘ እና የጉልበቴ ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ያወኩበት ነው፡፡ በተለይም ጉልበትን በቀዶ ጥገና መታከም ለተጨዋቾች ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ እኔም ያ ነገር እንደሚደርስብኝ ገምቼ ትልቅ ሀዘን ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና ምንም ነገር ሳይነካኝ በማሳጅ እና በመርፌ ብቻ መዳን እንደምችል ሀኪሞቹ ነግረውኝ ነው የተመለስኩት፡፡ አሁን የህመሙ መጠን እጅግ በጣም ቀንሶልኛል፡፡ በቀጣይ ሳምንታትም የሀኪሞቼን ምክር ሰምቼ ቀለል ያሉ ልምምዶችን የምጀምርና የምወደውን ክለቤን ማገልገል የምጀምር ይሆናል፡፡» ሲል ጨምሮ ገልጿል፡፡

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani man [675 days ago.]
 Sala anbesawe የዋልያዎቹና የፈረሰኞቹ የኋላ ደጀን get well soon our heroooooooo !

bikila [674 days ago.]
 bravo salah ayizoh hulum neger begizew yihonalna bizum lalefut negeroch atasbbachew .salah kewaliyawochu gar yehuala dejen honeh bemulu akuamna ethiopiwi wene yemitchawetew kuas egnam adnakiwochihn kemeda sinatah kir asegntonal.salah alh kale minm atihonmna ayizoh. wede medabachre gize temeliseh mayetna kilebihnna kemanm belay agerhn lemageligel tibeka zenda mignote new.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!