በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ቅዱሳኖቹ እሁድ በካምቦሎጆ ይጫወታሉ ጨዋታውን የሶማሊያ ዳኞች ይመሩታል
የካቲት 03, 2008

በይርጋ አበበ

በካፍ የ2016 የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ የአህጉሪቱ ከተሞች ይካሄዳሉ። ኢትዮጵያን በመድረኩ የሚወክለው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብም እሁድ በአስር ሰዓት ከሲሼልሱ ቅዱስ ሚካኤል ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወት ይሆናል። ሁለቱ ክለቦች ስያሜያቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቀዱስ ሚካኤል በመሆኑ ጨዋታውን የቅዱሳን ጨዋታ አስብሎታል።

እንደ ኢትዮጵያዊያን የዘመን ሰሌዳ በ2007 የኢትዮጵያን ፐሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን
የመወከል እድል በማግኘቱ ወደ አህጉረራዊ ውድድር የገባ ሲሆን በተመሳሳይ የሲሸልሱ ቀዱስ ሚካኤልም ያለፈው ዓመት
የአገሪቱ ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ ነው ለዚህ ውድድር የበቃው።

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ አሽኔ ትናንት ለዝግጅት ክፍላችን ባደረሱን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ፈረሰኞቹ ለዚህ ጨዋታ ዝግጅታቸውን በሚገባ አካሂደዋል። አቶ ኤርሚያስ በክለባቸው መግለጫ ጨምረው “የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሀዋሳ ስታዲየም እንዲሆን ታስቦ የነበረ ቢሆንም የጨዋታው ኮሚሽነር የጨዋታውን ስታዲየም መመልከት ከሚገባቸው ቀን ዘግይተው በመድረሳቸው የሀዋሳን ስታዲየም ማየት አልቻሉም። በመሆኑም ጨዋታው አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ እንዲሆን ተወስኗል። ጨዋታውን የሚመሩት ረወጨዳትና ዋና
ዳኞችም ከሶማሌ ናቸው። ኮሚሽነረዩ ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ናቸው” ብለዋል።

የፈረሰኞቹንና የሲሼልሱን ክለብ ጨዋታ በዋና ዳኝነት የሚመሩት ዋና ዳኛ ሀሰን መሀመድ ሃጂ ከማል ከዚህ ቀደም
ደደቢት በአሰልጣም ዮሃንስ ሳህሌ እየተመራ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ከሌላው የሲሼልስ ክለብ ግሪ ዎልቭስ ጋር
ሲጫወት ጨዋታውን የመሩ ዳኛ ናቸው።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ጋጣሚ ሆኖ የቀrበው ቅዱስ ሚካኤል በ1996 እ.ኤ.አ እንደተመሰረተ ይነገራል። ሆኖም ክለቡ በአገሪቱ ሊግ ከፍተኛ ታሪክ የተጎናጸፈ መሆኑን የውጤት ማህደሩ ያሳብቃል። 13 ጊዜያት የአገሪቱን ሊግ በበላይነት ያጠናቀቀ ሲሆን ሌሎች ታላላቅ አገራዊ ድሎችንም በሚገባ ማጣጣም የቻለ ክለብ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bikila [674 days ago.]
 wow des yemil sim kidus Mikael kekidus giyorgis sichawetu yeman degafi tihonaleh belugna tiru letechawetew new melise. hulet kidusanoch lene ekul nachewuna malete new abekahu kidus chewata yihunlachihu

Ashenafi Kebede [673 days ago.]
 Gooooood luck our belive club St.George fc Ethiopia Foot Ball Ambassador !!! VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV !!!

eliyas matahara [671 days ago.]
 st.kuratachin

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!