መከላከያ ከአል ማቃሳ የመጀመሪያው መጀመሪያ
የካቲት 05, 2008

በይርጋ አበበ

በአሰልጠጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥነው መከላከያ እግር ኳስ ክለብ የአፍረካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከአል ማቃሳ ጋር ያካሂዳል። ከሶስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ የውድድር መድረክ መቅረብ ችሎ የነበረው መከላከያ በወቅቱ ገና በመጀሪያው ዙር ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ክለቡ በዘንድሮው የአህጉራዊ ውድድር ግን ካለፈው ስህተቱ ትምህርት ወስዶ መቅረቡን አሰልጣኙ እና ተጫዋቾቹ ገልጸዋል።

ከሳምንት በፊት ጀምሮ ጠንካራ ዝግጅት ማድረጉን በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ከአንድ እጅ እጣት ያልበለጡ የድረ ገጽ የስፖርት ሚዲያዎች መካከል አንዱ ለሆነው “ሶከር ኢትዮጵያ ዶት ኔት” አስተያየታቸውን የገለጹት አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ቡድናቸው ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፍ እንደማይጠራጠሩ ተናግረው ነበር።

ከሶስት ወራት በፊት ከኢትዮፉትቦል ዶት ኮም ዘጋቢ ጋር ተገናኝቶ ስለ ቀጣይ የእግር ኳስ እቅዱ አስተያየቱን የሰጠው አማካዩ በሀይሉ ግርማ ወይም ባባ በበኩሉ “ያለሁት ከታላቅ ክለብ ጋር ነው። ከዚህ ክለብ ጋር ሆኜ በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ዋናው ግቤ ነው” ሲል ተናግሮ ነበር። ጨዋታው ዛሬ ከቀትር መልስ 10 ሰዓት ሲሆን በተለመደው አዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል።

የመከላከያ ተጋጣሚ የሆነው የግብጹ አል ማቃሳ በጠንካራው የግብጽ ሊግ ከዛማሌክ ጋር በነጥብ ተስተካክሎ በጎል ክፍያ ብቻ ተበልጦ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ መሆኑ እና የፊት መስመሩ ጠንካራ መሆን ለመከላከያ ትልቅ መልዕክት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በአንጻሩ ተከላካይ ክፍሉ በቀላሉ የሚያፈስ መሆኑ ደግሞ በባዬ ገዛኸኝና ሙሉዓለም ጥላሁን የሚመራው የመከለካያ አጥቂ ክፍል ደጋግሞ ማንኳኳት ከቻለ ከአንድም ሁለት ሶስቴ ሊከፈትለት ይችላል። ምክንያቱም አል ማቃሳ በዚህ ዓመት ባካሄዳቸው 17 የሊግ ጨዋታዎች 15 ሲገባበት ማግባት የቻለው ደግሞ 26 ነው። ይህ የሚያሳየው ደግሞ የፊት መስመሩ በርትቶ ሲያገባ የኋላው ደግሞ ተደራጅቶ የሚገባበት መሆኑን ነው።

መከላከያ በዚህ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ እና በጥሎ ማለፉ ባካሄዳቸው ከአስር ያላነሱ ጨዋታዎች የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆን የቻሉት አጥቂዎቹ ምንይሉ ወንድሙ እና ባዬ ገዛኸኝ እንዲሁም አማካዮቹ ፍሬው ሰለሞን እና በሀይሉ ግርማ ሲሆኑ የቡድኑ የተከላካይ መስመር ከፍተኛ ጥገና የሚያስፈልገው መሆኑ ታይቷል። በተለይ ከወላይታ ድቻ በዚህ ዓመት መከላከያን የተቃቀለው ወጣቱ ባዬ ከቅርብ ሳመንታት ወዲህ ወደ ቀድሞ ብቃቱ እየተመለሰ መሆኑን በሚያገባቸው ጎሎች እያስመሰከረ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!