ሊጉ ዛሬ በቡና ደርቢ ይቀጥላል
የካቲት 10, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሃ ግብር ትናንት ከቀትር በኋላ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች መጀመሩ ይታወቃል። የምስራቅ ኢትዮጵያው ድሬዳዋ ከነማ በፈቃዱ ታደሰ ብቸኛ ጎል ኤክትሪክን አሸንፎ የነጥብ ድምሩን 16 ማድረስ የቻለ ሲሆን ደደቢት በበኩሉ ሀዋሳ ከነማላይ ሶስት ጎሎችን አዝንቦ ደረጃውን ማስጠበቅ ችሏል።

ሊጉ ዛሬ ቅዳሜ እና እሁድም ቀጥሎ ይውላል። ዛሬ አርባ ምንጭ ላይ አርባ ምንጭ ከነማ የውጤት ቀውስ ውስጥ ያለውን ዳሽን ቢራን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ያስተናግዳል። አርባ ምንጭ ከነማ በዘጠኝናው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዳሽን ቢራ ደግሞ በደደቢት በተመሳሳይ አንድ ለባዶ ተሸንፈው ነ ወደ አስረኛው ሳምንት የተሸጋገሩት። አርባ ምንጭ ላይ የተቆጠረውን አዳነ ግርማ ጎነደር ላይ የገባውን ደግሞ ሌላው የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት ከአዳነ ግርማ እና ታፈሰ ተስፋዬ ጋር የሚመራው ሳሙኤል ሳኑሚ ነበር ያስቆጠረው።

በጥሎ ማለፉ ዋንጫ ደግሞ አርባ ምንጭ የዘወትር ተቀናቃኙን ሀዋሳ ከነማን አንድ ለባዶ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ራሱን በስነ ልቦና ሲያነሳሳ ዳሽን በበኩሉ በሲዳማ ቡና ተሸንፎ ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ዛሬ ሁለቱ ቡድኖች መሸናነፍ ከቻሉ የደረጃ ሰንጠዡ ላይ ለውጥ መፍጠር ያስችላቸዋል።

ከአመሻሹ 11 ፡30 ሲሆን ካምቦሎጆ የቡና ደርቢን ያስተናግዳል ኢትዮጵያ ቡናን ከሲዳማ ቡና። ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ጨዋታ አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ 11ኛ ደረጃን የግሉ አድርጎታል። በዛሬው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በኩል ተከላካዩ አብዱልከሪም መሃመድ የቀድሞ ክለቡን ለመጀመሪያ ጊዜ በተቃራኒነት ይፋለማል።

አዳማ ላይ አዳማ ከነማ ከሆሳዕና ከነማ ጋር ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ይጫወታሉ። በቅርቡ በአንዳንድ የግል ጉዳዮች ምክንያት ስራቸውን የመልቀቅ ስጋት ተጋርጦባቸው የነበሩትና በመጨረሻም ከክለቡ አመራሮች ዋስትና በማግኘታቸው ስራቸው ላይ ለመቆየት የወሰኑት የአዳማ ከነማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቡድናቸውን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ዛሬ ማሸነፍ ከቻሉም የፈረሰኞቹ ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ መሪነታቸውን ማስመለስ ይችላሉ።

ሊጉን ፈረሰኞቹ በ22 ነጥብ አናት ላይ ሆነው ሲመሩት በድሬዳዋ ከነማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈው አዳማ ከነማ ሁለተኛ ነው። ደደቢት ደግሞ ሶስተኛ ሲሆን ሲዳማ ቡና አራተኛ ድሬዳዋ ከነማ አምስተኛ ሆነው ተቀምጠዋል። ግርጌውን አራቱ የደቡብ ክልል ክለቦች ማለትም አርባ ምንጭ ከነማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ሀዋሳ ከነማ እና ሆሳዕና ሀድያ ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያሉትን ደረጃዎች ተቆጣጥረዋቸዋል።

አዳነ ግርማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ታፈሰ ተስፋዬ ከአዳማ ከነማ እና ሳሙኤል ሳኑሚ ከደደቢት እኩል ሰባት ጎሎችን አስቆጥረው የከፍተኛ ጎል አግቢዎችን ደረጃ ይመራሉ። የኢትዮጵያ ቡናው ያቡን ዊሊያም አምስት ጎሎችን ይዞ ይከተላቸዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Bereket (Beka) [702 days ago.]
 Sidama Buna (Original Buna ) 3 - 1 Bulla Gellebba ( Dengay Kenema )

Gezegeta [700 days ago.]
 For Bulla Gellebba fc " አደገኛ ሲሉ ባርሴሎና መጣ ብዬ.... አደገኛ ሲሉ ማድሪድ መጣ ብዬ.... ....ለካስ ኤቬረዲ ናት የሳሪሷ ውርዬ ! እኔ የምለው ግን 2009 ብሄራዊ ሊግ ጨዋታዎች የት ነበር የሚደረጉት "

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!