ፕሪሚየር ሊጉ በአስረኛው ሳምንት
የካቲት 14, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሃ ግብር ካሳለፍነው ረቡዕ አመሻሽ ጀምሮ እስከ ትናንት እሁድ አመሻሽ ድረስ ባሉት አራት ቀናት በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ቀጥሎ ውሏል። ሊጉ በሰባት ጨዋታዎች ምን ምን ክስተቶች ተከናውነውበታል? የሚሉትን ነጥቦች ከዚህ በታች እንመለከታለን። ታችኞቹ ማሸነፍም ሆነ ጎል ማስቆጠር አልቻሉም መረብ መድፈር ተስኖት ባዶ ለባዶ ተለያይቷል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌው ላይ የተቀመጡት ሆሳዕና ሀድያ እና ሃዋሳ ከነማ በአስረኛው ሳምንት መርሃ ግብር ደረጃቸውን የሚያሻሽሉበት ወይም ነጥባቸውን ከፍ የሚያደርጉበትን ውጤት ማስመዝገብ ሳይችሉ ቀርተዋል። 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አርባ ምንጭ ከነማም ቢሆን በሜዳው ዳሽን ቢራን ቢያስተናግድም የሰው የደቡብ ክልል መዲና ክለብ የሆነው ሀዋሳ ከነማ ወደ አገሪቱ መዲና አዲስ አበባ መጥቶ ከደደቢት ጋር ተጫውቶ ሶስት ለባዶ ተሸንፎ ሲመለስ ሆሳዕና ሀድያ በበኩሉ ወደ ናዝሬት አቅንቶ በአዳማ ከነማ ሁለት ለባዶ ተሸንፎ ተመልሷል። ሁለቱ ክለቦች በደረጃው ግርጌ ላይ አሁንም እንዲቀመጡ ሲገደዱ ነጥባቸው ደግሞ የታችኛው አምስት የላይኛው ደግሞ ዘጠኝ ብቻ ነው። የተሸከሙት የጎል እዳም ሀዋሳ ስምንት ሆሳሽና አምስት የጎል እዳ አላቸው።

የአዲስ አበባ ክለቦችን በሜዳቸው ድል የነሱት ደቡባዊያኑ

 በሳምንቱ አጋማሽ ሀሙስ አመሻሽ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት የቡና ደርቢዎቹ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ሲሆኑ እንግዳው ክለብ ሲዳማ ቡና ባለ ሜዳውን ኢትዮጵያ ቡናን በበርካታ ደጋፊዎቹ ፊት ሁለት ለአንድ አሸንፎ አንገት አስደፍቶት ተመልሷል። የቀድሞውን መልካም የኳስ ፍሰት የተላበሰ አጨዋወቱን እና አምበሉን መስዑድ መሃመድን ወደ ሜዳ ይዞ ያልገባው ኢትዮጵያ ቡና ከጨዋታው በኋላ በተመዘገበው ውጤት የተበሳጩ የክለቡ ደጋፊዎችና አመራሮች ቁጣቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል።

ትናንት እሁድ ከቀትር በኋላ በተካሄደው የመከላከያ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ደግሞ በተመሳሳይ ወላይታ ድቻ ባለ ሜዳውን መከላከያን ሁለት ለአንድ አሸንፎት ተመልሷል። ድቻ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 13 በማድረስ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ በአንድ ጊዜ ስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። ለወላይታ ድቻ ጎሎቹን አምበሉ አላዛር ፋሲካ ከእረፍት በፊትና ከእረፍት መልስ ሲያስቆጥር ለመከላከያ ደግሞ መሃመድ ናስር በፍጹም ቅጣት ምት ነው ያስቆጠረው።

አዳማ ከነማ ወደ አሸናፊት የተመለሰበት ሳምንት

በዚህ የውድድር ዓመት ካካሄዳቸው ስምንት ጨዋታዎች አንዱንም ሳይሸነፍ ዘልቆ የነበረው አዳማ ከነማ በዘጠንኛ ሳምንት ጨዋታው በድሬዳዋ ከነማ ሁለት ለባዶ ተሸንፎ ነበር። በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው የስምጥ ሸለቆው ክለብ ግን በአስረኛው ሳምንት መርሃ ግብር በሜዳው ሆሳዕና ሀድያን አስተናግዶ በቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ቡና አጥቂዎች ሻኩሪ እና ታፈሰ ተስፋዬ ጎሎች ሁለት ለባዶ አሸንፏል። ውጤቱን ተከትሎም ለ24 ሰዓታት ሊጉን ከአናት ሆኖ መምራት ችሎ ነበር። ታፈሰ ተስፋዬ በሆሳዕና ሀድያ መረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ከአዳነ ግርማ እና ሳሙኤል ሳኑሚ በአንድ ጎል በልጦ የሊጉን ኮከብ ጎል አግቢዎች ደረጃ እንዲመራ አስችለዋለች።

አስር ጎሎች በአዲስ አበባ ስታዲየም

በአስረኛው ሳምንት ከተመዘገቡ ክስተቶች መካከል አንዱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄዱ ጨዋታዎች አስር ጎሎች የተቆጠሩበት ሳምንት መሆኑ ነው። በሳምንቱ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ አምስት ጨዋታዎች ተካሂደው አራቱ ጨዋታዎች በመሸናነፍ የተጠናቀቁ ሲሆን አንዱ ጨዋታ ብቻ ማለትም የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል። መሸናነፍ በታየባቸው አራት ጨዋታዎች አስር ጎሎች የተቆጠሩ ሲሆን በሶስቱ ጨዋታዎች ሶስት ሶስት ጎሎች ሲቆጠሩ በአንዱ ጨዋታ ማለትም ድሬዳዋ ኤሌክትሪክን ባሸነፈበት ጨዋታ ብቻ አንድ ጎል ብቻ ተቆጥሯል።

አዲስ አበባ ላይ ከተቆጠሩት አስር ጎሎች አንዱን ጎል የሀዋሳ ከነማው ዳንኤል ደርቤ በራሱ ጎል ላይ ሲያስቆጥር አራቱ ጎሎች ደግሞ የተቆጠሩት በሁለት ተጫዋቾች ነው። የወላይታ ድቻው አላዛር ፋሲካ እና የደደቢቱ ዳዊት ፈቃዱ በሳምንቱ ሁለት ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል። አንድ ጎል ደግሞ በፍጹም ቅጣት ምት ተቆጥሯል። የጎሉ ባለቤትም የመከላከያው መሀመድ ናስር ነው።

ክልል ላይ አዳማ ከነማ ሆሳዕና ሀድያን ሁለት ለባዶ ያሸነፈበትን ጨምሮ በአጠቃላይ በሳምንቱ 12 ጎሎች ተቆጥረዋል። ይህም ማለት በየጨዋታው በአማካይ 1.71 ጎል ማለት ነው። ዳሽን ቢራ ከአርባ ምንጭ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያካሄዷቸው ጨዋታዎች ጎል ያልተቆጠረባቸው ብቸኞቹ ጨዋታዎች ናቸው።

በአጠቃላይ አስረኛው ሳምንት በዚህ መልኩ ሲጠናቀቅ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ያምናው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብና 12 ንጹህ ጎል ሲመራ አዳማ ከነማ በነጥብ ተስተካክሎ በአራት ጎሎች ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ደደቢት፣ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከነማ ከሶስተኛ እሰከ አምስተኛ ደረጃ ያለውን ይዘዋል። ወላይታ ድቻ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የደረጃውን ግርጌ የመጨረሻ ሶስት ደረጃዎች የያዙት ሶስቱ የደቡብ ክልል ክለቦች ሲሆኑ እነሱም ሆሳዕና ሀድያ በአምስት፣ ሀዋሳ ከነማ በዘጠኝ እና አርባ ምንጭ ከነማ በአስር ነጥብ ነው የተቀመጡት።

ሊጉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ቀጥሎ ሲውል የሊጉ መሪዎች ፈረሰኞቹ ወደ ጎንደር ተጉዘው ከዳሽን ቢራ ጋር ይጫወታሉ። የውጤት ነገር አልሆንልህ ያለው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ወደ ምስራቅ ተጉዞ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ሲጫወት በደቡብ ደርቢ 12ኛ እና 13ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አርባ ምንጭ ከነማ እና ሀዋሳ ከነማ .ሀዋሳ ላይ ይጫወታሉ። ወላይታ ድቻ በሜዳው አዳማ ከነማን ያስተናግዳል። ሆሳዕና ሀድያ ኤሌክትሪክን ሲያስተናግድ ሲዳማ ቡና በበኩሉ ደደቢትን በሜዳው ይገጥማል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ብቸኛው ጨዋታ ደግሞ ንግድ ባንክ ከመከላከያ የሚያካሂዱት ጨዋታ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Bereket (Beka) [728 days ago.]
  Dire Dewa Kenema 3 - 0 Bulla Gellebba

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!