አቶ መኮንን ኩሩ የካፍ ኢንስትራክተር ሰርተፊኬት ተሰጣቸው
የካቲት 16, 2008በይርጋ አበበ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ የስድስት ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ ባለሙያዎችን የካፍ አንደኛ ደረጃ ኢንስትራክተር ማጽደቁን ገልጿል። በካፍ የኢንስትራክተርነት ደረጃቸው ከጸደቀላቸው መካከል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ኩሩ ናቸው።

አወዛጋቢ ቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኩሩ በተደጋጋሚ ጊዜ በሚያነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተለይተው የሚታወቁ ሲሆን በተለይ በቅርቡ “ከሀትሪክ ጋዜጣ” ጋር ባደረጉት ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ “ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድቀት አውቃለሁ የሚለው አላዋቂ መብዛቱ ነው” ሲሉ ተናግረው ነበር። ለዚህ ደግሞ ከጋዜጠኛው ጨምሮ ሌሎች አካላትም ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሰሞኑን ካፍ ለአንደኛ ደረጃ ኢንስትራክተርነት እውቅና የሰጣቸው አቶ መኮንን ኩሩ የኢትዮጵያ እግር ከስ ፌዴሬሽንን ላለፉት ሶስት ዓመታት በቴክኒክ ዳይሬክተርነት መርተዋል።

ካፍ ከአቶ መኮንን ኩሩ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በስፖርት ሳይንስ የዶክትሬት ድግሪ ባለቤት የሆኑትን የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ አስተናሪው ለዶክተር ጌታቸው አበበ፣ ለአቶ ሰውነት ቢሻው፣ ለአቶ አብርሃም ተክለሀይማኖት፣ ለአቶ አብርሃም መብራቱ እና ለአቶ አንተነህ እሸቴ እውቅና ሰጥቷል።  

ፌዴሬሽኑ በላከው መረጃ ጨምሮ እንዳስታወቀው ሌሎች በፌዴሬሽኑ ስር የሚገኙ ኢንስትራክተሮች በፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዳይሬክተር አማካኝነት የትምህርት ደረጃቸው እየታየ ይሰጣቸዋል ሲል አስታውቋል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!