አደማ ከነማ ለሁለተኛ ጊዜ ተሸነፈ
የካቲት 18, 2008

በይርጋ አበበ

ለአራተኛ ጊዜ የፕሮግራም ለውጥ ሲካሄድበት የቆየው የወላይታ ድቻ እና አዳማ ከነማ ጨዋታ በወላይታ ድቻ ሁለት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። አዳማ ከነማ ከሜዳው ውጭ ያደረገውን ጨዋታ አለማሸነፉም ሊጉን የመምራት እድሉን አበላሽቶበታል። ለአሸናፊው ወላይታ ቻ ጎሎቹን ከእረፍት በፊት መሳይ አጪሶ ሲያስቆጥር ከእረፍት መልስ ደግሞ ዮሴፍ ድንገቶ አስቆጥሯል። የአዳማ ከነማው አጥቂ ሚካኤል ጆርጅ እና የወላይታ ድቻው መሳይ አንጪሶ በቀይ ካርድ ከርድ የተባረሩ ተጫዋቾች ናቸው።

በአስረኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ድረስ መጥተው መከላከያን ሁለት ለአንድ ማሸነፍ የቻሉት ወላይታ ድቻዎች በ11ኛው ሳመንትም አዳማ ከነማን በማሸነፋቸው ደረጃቸውን ወደ ስድስተኛ ከፍ ማድረግ ሲችሉ ነጥባቸውንም 16 አድርሰውታል። ተሸናፊው አዳማ ከነማ በበኩሉ በነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Biruk Bogale [693 days ago.]
 Great victory for Dicha

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!