ቱርክ የገፋችው ዋሊድ ስዊድን ተቀብለዋለች
የካቲት 18, 2008

በይርጋ አበበ

ኢትዮጵያዊው የ29 ዓመት ተከላካይ ዋሊድ አታ ከቱርኩ ጌንስበርሊ ጋር የነበረውን ኮንትራት በስምምነት ማቋረጡን ተከትሎ ለወራት ክለብ አልባ ሆኖ ቆይቶ ሰሞኑን ወደ ስዊድን አቅንቶ ለኦስተርሰንድስ ክለብ ፈርሟል። ዋሊድ ዝውውሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ስዊድን መመለሱ እና ለኦስተርሰንድስ መፈረሙ እንዳስተሰተው ተናግሯል።

ዋሊድ አታ ለቱርኩ ዋና ከተማ ክለብ ጌንስበልጊ ለሶስት ዓመታት ለመጫወት ተስማምቶ ወደ አንካራ አምርቶ የነበረ ቢሆንም ከቱርኩ ክለብ የጠበቀው የተሰላፊነት እድል ዝቅተኛ በመሆኑ ነው ከክለቡ ጋር በስምምነት ፊርማውን የቀደደው። “ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ እፈልጋለሁ” በማለት ቀደም ሲል ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም አስተያየቱን የሰጠው ዋሊድ አታ ስለ ብሔራዊ ቡድን ቆይታው የተናገረው ነገር የለም።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!