ዳሽን ቢራ የሚያካሂዳቸውን ሁለት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጭ እንዲጫወት ተወሰነ
የካቲት 18, 2008

በይርጋ አበበ

የጎንደሩ ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ በአንደኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎቹን ከሜዳው ውጭ እንዲያደርግ ተወስኖበታል። ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ከሀዋሳ ከነማ ጋር በጎንደሩ አጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ሊያካሂዳቸው የነበሩትን ሁለት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጭ እንዲጫወት የተደረገ ሲሆን ከሀዋሳ ከነማ ጋር በባህር ዳሩ ብሔራዊ ስታዲየም እንዲጫወት ሲወሰን ከፈረሰኞቹ ጋር ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲጫወት መወሰኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጨዋታ ፕሮግራሞችን የመቀያየር ባህሉ የታወቀ ቢሆንም የመጫወታ ስታዲየሞችን ለምን መቀየር እንዳስፈለገው ግን ግልጽ አይደለም። የዳሽን ቢራ ጨዋታ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ለምን እንደተቀየረ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም። ዳሽን ቢራ በአስር ጨዋታ አስር ነጥቦችን ሰብስቦ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አደማ ከነማ 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!