ፈረሰኞቹ ሊዮፓርዶቹን በባህር ዳር ያስተናግዳሉ
የካቲት 29, 2008

በይርጋ አበበ

ለአፍሪካቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ ከወቅቱ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ሱፐር ካፕ የዋንጫ ባለቤት ከሆነው ከዴክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ሀያል ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ጋር የሚያካሂዱት የመጀመሪያ ጨዋታ በባህር ዳሩ ብሔራዊ ሁለዐገብ ስታዲየም እንደሚካሄድ ታወቀ። ለፈረሰኞቹ ቅርብ የሆኑ የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች እንዳረጋገጡልን ቅዱስ ጊዮርጊስ በባህር ዳር እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል።

ከአንደ ዓመት በፊት በተመሳሳይ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በባህር ዳሩ ሁለገብ ብሔራዊ ስታዲየም አካሂደው ያሸነፉት ፈረሰኞቹ ከማዜምቤ ጋር ለሚያካሂዱት ጨዋታ ዛሬ ጀምሮ ወደ ባህር ዳር እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

በሌላ ዜና የፈረሰኞቹ ተጋጣሚ ሊዮፓርዶቹ በአገራቸው የሊግ ጨዋታ ተጋጣሚያቸውን ሁለት ለባዶ ማሸነፋቸውን ኢትዮጵያዊው ሶከርኢትዮጵያ ዶትኔት ለንባብ አብቅቷል። ባለፈው ሳምንት ወደ ሀዋሳ ተጉዘው በሀዋሳ ከነማ የሁለት ለአንድ ሽንፈት ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ተመሳሳዩ ሽንፈት እንዳይገጥማቸውም ጥንቃቄ እንደሚጠበቅባቸው ይታወቃል።

ፈረሰኞቹ በርካታ ደጋፊ አለን ብለው ከመiሚገልጿቸው አካባቢዎች አንዱ ባህር ዳር ሲሆን ባለፈው ዓመት ከ80 ሺህ የማያንስ የከተማዋ እና አካባቢው ነዋሪዎች የፈረሰኞቹን ጨዋታ በስታዲየም ተገኝቶ ድጋፉን ሰጥቶ ነበር።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bikila [683 days ago.]
 mingizem sanjaw yegna new dilu yegna new. b.dar degmo beliyu huneta tezegajita titebikachihualech

Gizegeta [680 days ago.]
 Gooooood luck our believe club Ethiopian Foot Ball Ambassadar St.George fc VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV !

Ashenafi Kebede [680 days ago.]
 Good Luck St.George fc. Sanjawe 2 - 0 TP Mazembe

Elias Ke Bahirdar [677 days ago.]
 Really we are proud by St.George fc. Ethiopia has great club real foot ball ambassador. Viva St.George fc proud of Ethiopiaaaaaa !!!

Sami [677 days ago.]
 እጅግ በጣም ኮርቻለሁ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ! የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ: አሸናፊን ; አፍሪካን በመወከል የአለም ክለቦች ውድ ድር ላይ የተሳተፈውን የሱፐር ካፑ አሸናፊ የሆነውን ግዙፍ ክለብ ትላንትና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደዛ ሲያርበደብደው ማየት እንዴት ደስ ይላል :: ቅዱስ ጊዮርጊስ አኩርቶናል ገና ብዙ ነገር እንጠብቃለን ከዚህ ታሪካዊና አርበኛ ክለብ :: ሌሎቹም ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ነገር መማር ይችላሉ :: ጠንክረን ከሰራን እነ አል አህሊ - እነ ዛማሊክ - እነ ቲፒ ማዜምቤ የደረሱበት ደረጃ የማንደርስበት ምንም ምክንያት የለም Viva St.George fc Ethiopian Foot Ball Ambassador VVVVVVVVVV !!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!