ዋልያዎቹ የመጀመሪያልምምዳቸውን በ15 ተጫዋቾች ጀመሩ
መጋቢት 07, 2008

በይርጋ አበበ

በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። አሰልጣኙም ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
ከአንዳንድ ምንጮች በደረሰን መረጃ መሰረት የመከላከያው ሙሉዓለም ጥላሁን መጠነኛ ጉዳት ስለገጠመው የዛሬውን ልምምድ ካለመስራቱ በስተቀር ሶስቱን ግብጠባቂዎች ጨምሮ 15 ተጫዋቾች ግን ልምምዳቸውን ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት
ጀምሮ አካሂደዋል። አምስቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ክለባቸው ከቲፒ ማዜምቤ ጋር ላለበት የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ኮንጎ የሚያመሩ ሲሆን ከኮንጎ መልስ ግን ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አምበሉ ማን ይሆናል?

ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስንብት በኋላ አገሩን በአምበልነት ሲመራ የቆየው ሳላዲን ሰይድ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደረሰበት ጉዳትና የብቃት መውረድ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ከተቀነሰ በኋላ ግን ዋልያውን በአምበልነት ሲመራ የቆየው ታታሪው ተከላካይ ስዩም ተስፋዬ ነው። አሁን ደግሞ አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳላዲን ሰይድን ወደ ቡድናቸው መጥራታቸውን ተከትሎ ከሁለቱ የትኛው ቋሚ አምበል ይሆናል የሚለው ጥያቄ ይነሳል።

ሳላዲን ሰይድ ባልተገኘባቸው የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ቡድኑን በአምበልነት መምራት የቻለው የፈረሰኞቹ በሀይሉ አሰፋ ቢሆንም በሀይሉም ከብሔራዊ ቡድኑ ከተቀነሰ በኋላ አሰልጣኝ ዮሃንስ እምነታቸውን የጣሉበት በስዩም ላይ
ሆኗል። በሀይሉ አሰፋም ሆነ ሳላዲን ሰይድ ብሔራዊ ቡድኑን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ከስዩምና ከሳላዲን የትኛው በአምበልነት ይመራል ለሚለው ጥያቄ መልሱን ከአሰልጣኙ መስማት የሚጠበቅብን ቢሆንም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ግን ከአጥቂው ይልቅ ለተከላካዩ የአምበልነቱን ምልክት ይሰጡታል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኙ በተለይ በደደቢት በነበሩበት ወቅት ከስዩም ጋር አብረው መስራታቸውን ተከትሎ እና ስዩምም ለረጅም ዓመታት ብቃቱን ጠብቆ መጫወቱን ተከትሎ የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን እምነት ለማግኘት አይቸገርም ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Melaku [640 days ago.]
  Useless pooooooor and looooooser coach Yohanes ! please leave us !!! we didnt excepect any good thing from Yohanes !

Samiflex [640 days ago.]
 እኔ የማዝነው የምናደደው በማይችል ኮች እየሰለጠነች ላለችው ሃገሬ ነው ሃገራችን ላይ ለተዘጋጀ ደካማ ውድድር CECAFA እንኳን ቡድን መስራት ያልቻለ አሰልጣኝ ምኑን አሰልጣኝ ሆነው Yohanes !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!