የዋልያዎቹ ተፋላሚ አልጀሪያ እና የቡድን ስብስቧ
መጋቢት 08, 2008

በይርጋ አበበ

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አስር አባት ሆና ከኋላዋ ኢትዮጵያን ሌሴቶን እና ሲሸልስን ያሰለፈችው የሰሜን አፍሪካዋ አጄሪያ በምድቡ ሁለት ጨዋታዎች ሁለቱንም በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት እየመራች ትገኛለች።

የበርሃ ተዋጊዎቹ መጋቢት 16 በሜዳቸው እና መጋቢት 20 ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ለሚያካሂዷቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች 23 ተጫዋቾችን መርጠዋል። አሰልጣኝ ክርስቲያን ጉርኩፍ የሚመሩት የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አብዛኛው ስብስቡ ትውልደ ፈረንሳያዊያን ሲሆኑ በክለብ ፉት ቦላቸውም አብዛኞቹ የሚጫወቱት ለአውሮፓ ክለቦች ነው። በአገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱት አራት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው። ከአራቱ የአገር ውስጥ ተጫዋቾች መካከል ሁለቱ ግብ ጠባቀዎች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ተከላካዮች ናቸው።

በዋልያዎቹ በኩል ቀድመው ከተጠሩት ሽመልስ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ በተጨማሪ ዘግይቶ ጥሪ የተደረገለት ዋሊድ አታ ብቻ ከአገር ውጭ ባሉ ሊጎች የሚጫወቱ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 21 ተጫዋቾች ግን በአገር ውስጥ ነው የሚጫወቱት።  

ፈረንሳያዊው የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ክርስቲያን ጉርኩፍ ቡድናቸውን ያዋቀሩት ከአልጄሪያ ከግሪክ ከስፔን ከፈረንሳይ ከፖርተጋል ከጣሊያን እና ከእንግሊዝ ሊጎች በሚጫወቱ ተጫዋቾች ነው። ይህም ማለት በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ቶፕ አምስት የአውሮፓ ሊጎች ከሚባሉት ጀርመን፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን፣ ጣሊያን እና እንግሊዝ ሲሆኑ የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ያላካተተው በጀርመን የሚጫወት ተጫዋች ብቻ ነው ማለት ነው።

ተጠባቂ ተጫዋች ሪያድ ማሃሬዝ

ከሁለት ዓመታት በፊት ለፈረንሳዩ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለብ ሌ ሃርቭ ይጫወት የነበረውና ከወራት በፊት ደግሞ የዝውውር ሂሳቡ 400 ሺህ ፓውንድ ብቻ የነበረው ሪያድ ማሃሬዝ በአሁኑ ወቅት በምድረ አውሮፓ በችሎታው የሚደነቅ ተጫዋች ሆኗል። ጉልበትንና ፍጥነትን ከተሟላ የቴክኒክ ችሎታ ጋር አጣምሮ የያዘው የሌስተር ሲቲው አጥቂ ያለምንም ጥርጥር የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ቁልፍ ሰው ነው ማለት ይቻላል።

ፍርሃት የማይሰማውና ለተጋጣሚ ተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ፈተና የሆነው ይሄው ሞገደኛ አጥቂ ለዋልያዎቹ ተከላካይ ክፍል ትልቅ የቤት ስራ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ተጫዋቹ ሜዳ ላይ ያለውን ሁሉ ለመስጠት የማይሰንፍ ሲሆን ፍጥነቱና የጎል አጨራረሱም የተዋጣለት ነው። በአንድ ለአንድ ፍልሚያም ሆነ በጀብደኝነት በርካቶችን አታሎ በማለፍ የተካነ ሲሆን ለቡድን አጋሮቹ ሰፊ የመጫወቻ ክፍተትን በመፍጠርም የተመሰከረለት ነው። ለዚህ ደግሞ በክለብ ፉትቦሉ ከሌስተር ሲቲው የቡድን አጋሩ ጆኒ ቫርዲ ጋር የፈጠሩት ጥምረት አስረጂ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።

ከማሃሬዝ በተጨማሪ ደግሞ በዚህ ዓመት መጠነኛ መቀዛቀዝ የታየበት የፖርቶው ያሲን ቤራሂሚ ሌላው የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ነው። በአሰልጣኘ ማሪያኖ ባሬቶ ዘመን ወደ አዲስ አበባ መጥቶ አንድ ጎል አግብቶ የተመለሰው የፐፖርቶው አጥቂ በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ለሚመራው የዋልያዎቹ ስብስብም ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
m.d [665 days ago.]
 etc

arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!