ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ዛሬ ይጀመራል
መጋቢት 12, 0008

በይርጋ አበበ

በሙገር ሲሚንቶ ስኬታማ ጊዜን ያሳለፉት ውጤታማው አሰልጣኝ ግርማ ሀይለዮሃንስ እንዲያሰለጥኑት የተደረገው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ልምምዱን እንደሚጀምር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ አመለከተ። ቡድኑ 38 ተጫዋቾችን በጊዜያዊነት የመረጠ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡናው እያሱ ታምራት ይገኝበታል።

ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የኑሚያካሂድ ይሆናል። ለዚህ ጨዋታ ዝግጅትም ዛሬ መጋቢት 12 ቀን እንደሚጀመርና ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ ተጫዋቾችን የያዙ ክለቦች ተጫዋቾቹን በጊዜ እንዲለቁ ፌዴሬሽኑ ለክለቦቹ ደብዳቤ መጻፉን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!