“የፈረሰኞቹ ፍልሚያ ለዋልያው የሞራል ስንቅ ሊሆን ይችላል” አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ
መጋቢት 13, 2008

በይርጋ አበበ

የአፍሪካ የወቅቱ ቁጥር አንድ ክለብ የሆነው ቲፒ ማዜምቤ ከአፍሪካ ቀዳሚ ታሪክ ካለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባህር ዳር ላይ እና ሉሙምባሼ ላይ ተጫውቶ ሶስት አግብቶ ሁለት ገባበት። ሁለቱ ቡድኖች ከመጫወታቸው በፊት የበርካታ ስፖርት አፍቃሪ ቤተሰብ ትንበያ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ቡድን በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ፍጹም የበላይነት እንደሚወስድ ነበር። በዚህም መሰረት ቲፒ ማዜምቤ ወደ ቀጣዩ ዙር በቀላሉ ያለፈ ክለብ አድርገው ቆጥረውት የነበረ ቢሆንም በበሀይሉ አሰፋ የሚመራው የፈረሰኞቹ የመሃል ክፍል ለማዜምቤ ተከላካይ ክፍል ፍጹም ራስ ምታት ሆኖበት ተገኘ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ180 ደቂቃዎች ለምዕራብ አፍሪካው ቡድን ፈታኝ ሆኖ መገኘቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ዓርብ እና የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ከአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ጥሩ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ተናግረዋል። ብሔራዊ ቡድኑ ትናንት ምሽት ወደ ግብጽ ካይሮ አቅንቶ ከስምንት ሰዓታት የኤርፖርት ቆይታ በኋላ ወደ አልጄርስ ይጓዛል። ቡድኑ ከኢትዮጵያ ከመነሳቱ በፊት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ዮሃንስ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳስታወቁት የፈረሰኞቹ ድል ብሔራዊ ቡድኑን ከማነሳሳቱም በላይ የፈረሰኞቹ ተጫዋቾች ለቡድኑ ወሳኝነታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። አሰልጣኙ በጋዜጣዊ መግለጫቸው “የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች የአካል ብቃታቸውና ጤንነታቸውን ሳያረጋግጡ ወደ አልጄሪያ ይዘው ከማቅናት ለምን በሌሎች ተጫዋቾች ቡድነዎን አላጠናከሩም?” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጡም “እኛ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ አልቻልንም። የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ግን ቢያንስ ሁለት ኢንተርናሽናል ጨዋታ አድርገዋል። ይህ ደግሞ ቡድኑን በሚገባ ይጠቅምልናል ብለን እናስባለን። የጤንነታቸውን ጉዳይ አስመልክቶ ለጠየከው ጥያቄ መቼም አራቱም ተጫዋቾች በአንድ ጊዜ ሊጎዱ እንደማይችሉ እርግጠኞች ነበርን። ቢጎዱብን እንኳ ወደ አልጀሪያ ይዘን መሄድ ከነበረብን 18 ተጫዋቾች በተጨማሪ ሶስት ተጫዋቾችን ስለያዝን የሚያሰጋን ነገር የለም” ብለዋል።

አሰልጣኙ በወቅቱ ስለ ሳላዲን ሰይድ ከብሔራዊ ቡድን ውጭ መሆን ስለ አስራት መገርሳ አምበል መሆን እና ሌሎች ወቅታዊና ቡድኑን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው መልስ ሰጥተውበታል። የአሰልጣኙን መግለጫ ሙሉ ክፍል ይዘን እንመለሳለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Brhanu [394 days ago.]
 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጀርያ የሚያደርጉት ጫወታ መልካም እድል ይሁንላቸው!! ግን ሳላህዲን ሰይድ ኣለመሰለፉ ኣሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ችግር ኣላቸው!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!