በሁለት ቀናት ከአልጄሪያ ጋር
መጋቢት 15, 2008

በይርጋ አበበ

ካሜሩን እና ጋቦን ቀጣዮቹን የአፍሪካ ዋንጫዎችን የሚያዘጋጁ አገሮች ናቸው ካሜሩን የሴቶችን ጋቦን የወንዶችን። በእነዚህ አገራት ለሚካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች በሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያካሄዱ ያሉት ከአልጄሪያ ጋር መሆኑ አጋጣሚውን ለየት ያደርገዋል።

ወንዶቹ ነገ ከምሽቱ 4፡30 ሲሆን በአልጄሪያዋ ዋና ከተማ አቅራቢያ በምትገኘዋ ቢላድ ከተማ ሲያካሂዱ ሴቶቹ ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ አስር ሰዓት ያካሂዳሉ። የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ወደ አልጄርስ አቅንቶ አንደ ለባዶ ተሸንፎ የተመለሰ ሲሆን በቅዳሜው ጨዋታ ውጤት ለመቀልበስና ወደ መጨረሓው ዙር ለማለፍ የአገሩን ደጋፊዎች የተማመነ ይመስላል። ወንዶች በበኩላቸው ገና ከጅምሩ በአውሮፕላን ጉዞ መስተጓጎልና በዝግጅት ጊዜ ማነስ እንዲሁም የተጫዋቾች ተሟልቶ አለመገኘት ነገ ምሽት ለሚያካሂዱት ጨዋታ ሳንካዎችን ሲጋፈጡ ቆይተዋል።

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድናቸውን ይዘው ወደ አልጄሪያ ከማቅታቸው በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት የቡድናቸው ዓላማ የተቻለውን ሁሉ አድርጎ የቡድኑን ሞራል የማይጎዳ ውጤት የዞ መመለ መሆኑን ገልጸው ነበር። ለዚህ ደግሞ ቡድናቸውን በስነ ልቦና ሲያዘጋጁ መቆየታቸውንም አስታውቀዋል።

ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዝግጅት ክፍልም ለሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖቻችን መልካም ውጤት እየተመኘ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደውን የሴቶች ብሔራዊ ቡድናችንን ጨዋታ ደጋፊው በስታዲየም ተገኝቶ ቡድኑን እንዲያበረታታ እናስታውቃለን። የወንዶች ብሔራዊ ቡድነ ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ሲካሄድም እንደተለመደው በስታዲየም ተገኝተው ድጋፋቸውን ለቡድኑ እንዲለግሱ ጥሪውን ያቀርባል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!