የሆሳዕና ሀድያ ወቅታዊ እንቅስቃሴ የዘገዬ ወይስ የረፈደ?የሆሳዕና ሀድያ ወቅታዊ እንቅስቃሴ የዘገዬ ወይስ የረፈደ?
መጋቢት 25, 2008

የሆሳዕና ሀድያ ወቅታዊ እንቅስቃሴ የዘገዬ ወይስ የረፈደ?
በይርጋ አበበ

 የደቡብ ክልልን ወክለው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደሩ አምስት ክለቦች መካከል አንዱ በዚህ ዓመት ሊጉን የተቀላቀለው ሆሳዕና ሃድያ ይገኝበታል። የሆሳዕና ከተማው ክለብ ሊጉን በተቀላቀለበት ዓመት የመውረድ ስጋት ያንዣበበት ሲሆን ይህ የመውረድ ስጋቱ የገጠመው ደግሞ ገና የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ ጀምሮ ነው። ይህን ስጋቱን ዘግይቶ የተረዳ የሚመስለው የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ የሊጉ ሁለተኛ ዙር ከመጀመሩ በፊትት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ስድስት ተጫዋቾችንና ሁለት አሰልጣኞችን አዘዋውሯል። ለመሆኑ እነማንን አዘዋወረ እና በዝውውሩ ምን አዲስ ነገር ሊፈጠር ይችላል ለሚሉት ጥያቄዎች ከዚህ በታች በስፋት ተዘርዝሯል።

አዲሶቹ ፈራሚዎች

የሆሳዕና ሀድያ እግር ኳስ ክለብ ባሳለፍነው ሳምንት ካሳለፋቸው ታላላቅ ውሳኔዎች መካከል የቀድሞውን የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን በዋና አሰልጣኝነት መቅጠሩ ይገኝበታል። የቀድሞውን የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሳዳት ጀማልን ደግሞ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯለ።

ከእነዚህ በተጨማሪ ደግሞ አምስት የአገር ውስጥ እና አንድ አፍሪካዊ ተጫዋቾችን በጅምላ አስፈርሟል። ክለቡ በዚህ ሳምንት ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ከሀዋሳ ከነማ የተሰናበቱት መስቀሌ መንግስቱ እና ወንድማገኝ ተሾመ፣ ቢኒያም ታዬ፣ አሸናፊ አደም፣ አልፋየሁ ሙላት እና ሌላው ስሙ ያልተጠቀሰ አፍሪካዊ ተጫዋች ናቸው።

የክለቡ ቀጣይ ጉዞ

አዲሱ የሆሳዕና ሀድያ አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ ከደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት አጠር ያለ ቆይታ ዓላማቸው ክለቡን ከመውረድ መታደግ መሆኑን ተናግረዋል። ክለቡ ግን በመጀመሪያው ዙር ካካሄዳቸው 13 ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻለው አምስት ነጥቦችን ብቻ ሲሆን ተጨማሪ ዘጠኝ የጎል እዳም አለበት።  ከሆሳዕና ቀጥሎ ያሉትን የወራጅ ቀጠናውን ደረጃዎች የያዙት ቡድኖች ኢትዮጵያ ቡና አርባ ምንጭ ከነማ እና ዳሽን ቢራ ሲሆኑ እነዚህ ክለቦች ደግሞ እያንዳንዳቸው በቅደም ተከተል 15 14 እና 13 ነጥቦችን ይዘዋል። ዳሽን ቢራ ደግሞ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሲሆን ተስተካካይ ጨዋታውን የፊታችነ ረቡዕ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተጫውቶ ካሸነፈ ነጥቡን ወደ 16 ማሳደግ ስለሚችል ለሆሳዕና ከነማ ከባድ ፉክክር ይፈጥርበታል።

አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ  ክለቡን ከወራጅነት ለመታደግ እንሰራለን ቢሉም የክለቡ የወቅቱ ውሳኔ ግን የረፈደ ምናልባትም የዘገየ እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል።

በተያያዘ ዜና ሀዋሳ ከነማ የዳዋ ሁጤሳን ዝውውር ማጠናቀቁን ከሀዋሳ የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ዘግበዋል። ሀዋሳ ከነማን በጊዮርጊስ ቦታ ያጣውን አጥቂ ለማስፈረም ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ መክፈሉ ተገልጿል። ሀዋሳ ከነማ አራቱን አጥቂዎቹን በተለያዬ ምክንያት ካሰናበተ በኋላ ቡድኑ ውስጥ ሁለት አጥቂዎች ብቻ የያዘ በመሆኑ ቀደም ብሎም የአጥቂ ችግር እንዳለበት ሲነገር በመቆየቱ የዳዋ ዝውውር የክለቡን ችግር ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዳዋ ሁጤሳ ከአንድ ዓመት በፊት ከድሬዳዋው ናሽናል ሴሜንት ክለብ ፈረሰኞቹን የተቀላቀለ ሲሆን ለፈረሰኞቹ ከመፈረሙ በፊት የልጁን ችሎታ የተመለከቱት ፖርቹጋላዊው የዋልያዎቹ አሰልጣኘ የነበሩት ማሪያኖ ባሬቶ ናቸው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Daniman [621 days ago.]
 ጥያቄ ?????? እባካችሁ ኢትዮ ፉትቦሎች እቺን ጥያቄዬን መልሱልኝ የኔ ጥያቄ የዳዋ ሁጤሳ ዝውውር ላይ ነው ልጁ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ውሉ አላለቀም ሃዋሳ ከነማ ለፊርማ ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ መክፈሉ ተገልጿል ታዲያ ጊዮርጊስ ከዚህ ገንዘብ ላይ ያገኘው ነገር አለ ? ወይስ ጊዮርጊስ በነፃ ነው የለቀቀው please ጥያቄዬን መልሱልኝ ?!!!

Daniman [620 days ago.]
 Reminder....... እባካችሁ ኢትዮ ፉትቦሎች እቺን ጥያቄዬን መልሱልኝ የኔ ጥያቄ የዳዋ ሁጤሳ ዝውውር ላይ ነው ልጁ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ውሉ አላለቀም ሃዋሳ ከነማ ለፊርማ ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ መክፈሉ ተገልጿል ታዲያ ጊዮርጊስ ከዚህ ገንዘብ ላይ ያገኘው ነገር አለ ? ወይስ ጊዮርጊስ በነፃ ነው የለቀቀው please ጥያቄዬን መልሱልኝ ?!!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!