በ17ኛው ሳምንት ፈረሰኞቹ ወደ ምስራቅ ሲያቀኑ ቡና ከኮረንቲ ይጫወታልበ17ኛው ሳምንት ፈረሰኞቹ ወደ ምስራቅ ሲያቀኑ ቡና ከኮረንቲ ይጫወታል
ሚያዚያ 24, 2008


በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ በሚካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች ይቀጥላል። ኢትዮጵያ ቡና ያለ ዋና አሰልጣኙ ከኤሌክትሪክ ጋር ይጫወታል።

ፕሪሚየር ሊጉ ነገ ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ ከንግድ ባነክ ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ከወላይታ ድቻ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከነማ ከመከላከያ በተመሳሳይ ሰዓት ክልል ላይ ሲጫወቱ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ደደቢት ከአዳማ ከነማ በዘጠኝ ሰዓት ይጫወታል። በቅርቡ ከስራ እስኪያጁ ጋር የተለያየውና ዋና አሰልጣኙም በህመም ምክንያት ነገ ቡድናቸውን የማይመሩለት ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከአመሻሹ 11፡30 ሲሆን በተከታታይ ሶስት ጨዋታ ከተሸነፈው ኤሌክትሪክ ጋር ይጫወታል።

ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች በጉንፋን ህመም ምክንያት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከክለቡ ካምፕ አቅራቢያ ከሚገኝ ሰናይ ሆስፒታል ገብተው ክህምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ነገ ቡድኑ ኤሌክትሪክን ሲገጥም ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ቡድናቸውን የማይመሩ ይሆናል ቡናም በምክትል አሰልጣኝ እየተመራ ይገባል። የክለቡ ምንጭ አያይዞ እንደገለጸልን በቅርቡ ከኃላፊነት የተነሱትን ስራ አስኪያጅ የአቶ ገዛኸኝ ወልዴን ቦታ ለመተካት አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ክለቡ አውጥቷል። ለክለቡ ቴክኒክ ዳይሬክተርም የቅጥር ማስታወቂያ መውጣቱ ተገልጿል።

ደደቢት ከአዳማ ከነማ ጋር የሚያካሂዱት ጨዋታ ለዛሬ ቀጠሮ የተያዘለት ቢሆንም በፋሲካ በዓል ምክንያት ወደ ማክሰኞ እንዲዘዋወር ያደረገው ፌዴሬሽኑ መሆኑን ከሳመንት በፊት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በአንድ ቀን ሁለት ጨዋታዎች ከተካሄዱ ከስታዲየም የሚገኘው ገቢ ለሁለቱ ባለሜዳ የሆኑ ክለቦች ይሆናል። በዚህም መሰረት ነገ ደደቢት አዳማ ከነማን ዘጠኝ ሰዓት ላይ ካስተናገደ በኋላ ቡና ባለሜዳ ሆኖ ኤሌክትሪክን ያስተናግዳል። ስለዚህ የስታዲየሙ ገቢ ለሁለቱ ክለቦች እና ለፌዴሬሽኑ ይሆናል ማለት ነው። ሆኖም ግን ፌዴሬሽኑ ቀድሞ ደደቢት ሰኞ እንዲጫወት ፕሮግራም በማውጣቱ ማክሰኞ እንዲጫወት ሲወስን የሁለቱን ክለቦች የስታዲየም ገቢ በተመለከተ ያሳወቀው መግለጫ የለም።

ሊጉን ከላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ33 ሲመራ ከታች ሀድያ ሆሳዕና በስድስት ነጥብ ይመራዋል።  የኮከብ ጎል አግቢነቱን ደረጃ የአዳማ ከነማው ታፈሰ ተስፋዬ አስር ጎሎችን ይዞ ሲመራ የፈረሰኞቹ ምክትል አምበል አዳነ ግርማ እና የኢትዮጵያ ቡናው ያቡን ዊሊያም በዘጠኝ ጎሎች ይከተሉታል።ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bcfgudmp [624 days ago.]
 1

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!