በክለቡ አመራሮች “የእግዚያብሔር ስጦታ” የተባለው ያቡን ዊሊያም የክለቡን ደጋፊዎች አደነቀበክለቡ አመራሮች “የእግዚያብሔር ስጦታ” የተባለው ያቡን ዊሊ
ሚያዚያ 24, 2008


በይርጋ አበበ

በዚህ ዓመት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የኢትዮጵያን እግር ኳስ የተዋወቀው ካሜሩናዊው አጥቂ ያቡን ዊሊያም ከሶከር ኢትዮጵያ ዶትኔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የክለቡን ደጋፊዎች አድንቋል። የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ በበኩላቸው ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር ባደረጉት ቆይታ ተጫዋቹን አድንቀዋል።

ዊሊያም ስለደጋፊዎቹ “የሚገርሙ ናቸው በጣም ነው የምወዳቸው። የግድ እንድትጫወት ያደርጉሃል። በጣም ነው የሚያግዙህ። ደጋፊ የሌላቸው ክለቦች ጋር ልትጫወት ሜዳ ስትገባ ምንም የተለየ ስሜትና የማሸነፍ ተነሳሽነት አይኖርህም። የቡና ደጋፊዎች ግን ከሜዳቸው ውጭ ሳይቀር ይመጣሉ። ለምሳሌ አዳማ ከባለሜዳዎቹ በላይ የቡና ደጋፊዎች ይበዙ ነበር። ሜዳ ላይ ሲዘምሩ ስናያቸው አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን አምነን እንጫወታለን። የእኛ ደጋፊዎች የሚገርሙ ናቸው። ያነቃቃሉ” ሲል ገልጿቸዋል። በግልም የተከላካዩ አብዱልከሪም መሀመድ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳለው የገለጸ ሲሆን ከቡና ውጭ ደግሞ የቀድሞው የቡና የመስመር አጠቂ የነበረውን አስቻለው ግርማን ብቃት አወድሷል።

የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ በበኩላቸው “ተጫዋቹ የግል ባህሪው በጣም ቆንጆ ነው። ሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጭ የመነጫነጭና የመረበሽ ስሜት አይታይበትም። የታዘዘውን ብቻ የሚሰራ ተጫዋች ነው” ሲሉ የገለጹት ሲሆን አያይዘውም ወደ ክለቡ የተቀላቀለበትን መንገድ ሲገልጹ “የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን ጣጣዎች በሙሉ ጨርሶ የመጣ በመሆኑ የክለባችን አመራሮች ሳይቀሩ የእግዚያብሔር ስጦታ ነው ሲሉ ያሞግሱታል። በክለባችን ቤተሰብ ከሚወደዱ ተጫዋቾች ቀዳሚው ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ያቡን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ለፈረሰኞቹ ለመጫወት እንደነበር ይታወቃል።

ካሜሩናዊው አጥቂ በአሁኑ ሰዓት በቡና ክለብ ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ ከሚባሉት አይመደብም። ወርሃዊ ደመወዙም ከሁለት ሺህ ዶላር እንደማይበልጥ አቶ ሙሉጌታ ገልጸውልናል። በኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ያቡን ዊሊያምን ጨምሮ አምስት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ይገኛሉ።ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!