ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በድጋሚ በአቻ ውጤት ተለያ
ግንቦት 01, 2008

በይርጋ አበበ

ትናንት ከቀትር መልስ አመሻሹ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት ሁለቱ ተቀናቃኝ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ባዶ ለባዶ ተለያዩ። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ግንኙነታቸውም በተመሳሳይ ውጤት ነበር የተለያዩት። 

ቁጥር ስፍር የሌለው የሁለቱም ክለቦች ደጋፊ በስታዲየም ተገኝቶ የተከታተለው ይህ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ የጎል ሙከራ የበላይነትና በኢትዮጵያ ቡና የኳስ ቁጥጥር ፍጹም የበላይነት ነበር የተጠናቀቀው። በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ፈረሰኞቹ በሳላዲን ሰይድ አማካኝነት ያደረጉት ሙከራ ከግቡ አናት በቅርብ ርቀት የወጣባቸው ሲሆን አዳነ ግርማ የሞከረውና ከግብ ጠባቂው አልፋ መረብ ላይ ልታርፍ የነበረችውን ኳስ የቡናው ተከላካይ አብዱልከሪም መሀመድ ያዳነበት ሙከራ ተጠቃሽ ነው። በቡና በኩል ሳላምላክ ተገኝ የፈረሰኞቹን ተከላካዮች አታሎ ያሻገረለትን ኳስ ሳዲቅ ሴቾ በግንባሩ ገጭቶ አስቆጠረ ሲባል ከግቡ ቋሚ በቅርብ ርቀት የወጣበት ሙከራ ተጠቃሽ ነው። ከዚህ በተረፈ ግን የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ የተጠናቀቀው የቡናዎቹ ወጣት አማካይና ተከላካይ ተጨዋቾች በፈረሰኞቹ አቻዎቻቸው ላይ የኳስ ቁጥጥሩን የበላይነት የወሰዱበት ሆኖ ተጠናቋል።
St.George Vs Ethiopian Coffee

በሁለተኛው የጨዋታ ግማሽ በሀይሉ አሰፋን አስወጥቶ ጎድዊን ቺካን ያስገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ በበለጠ በተጋጣሚው ተበልጦ አምሽቷል። በተለይ ይህ ከውጭ አገር የመጣው አጥቂ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ጨዋታን በማንበብ በኩል የነበረበት ድክመት ለፈረሰኞቹ በጨዋታ መበለጥ ምክንያት ነው። ያም ሆኖ ግን አዳነ ግርማ በአስር ደቂቃ ልዩነት ሁለት ያለቀላቸው የጎል እድሎችን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም የጎሉን መስመር ለይቶ ባለማወቁ ኳሶቹ ባክነውበታል።
Ethiopian Coffee


በቡናዎች በኩል ደግሞ በተለይ ሳላምላክ ተገኝ፣ ኤሊያስ ማሞ፣ እያሱ ታምሩ እና አማኑኤል ዮሃንስ በፊት መስመር የፈጠሩት ልዩ ጥምረት ለፈረሰኞቹ ተከላካዮች አስቸጋሪ ሆነው እንዲያሹ አድርጓቸዋል። ከሶስቱ አማካይ አጥቂዎች በተጨማሪ ደግሞ የመስመር ተከላካዮቹ አብዱልከሪም መሀመድና አህመድ ረሺድ የነበራቸው ቁርጠኝነት ቡና በኳስ ቁጥጥር በልጦ እንዲያመሽ አድርገዋል። በቡና በኩል በጨዋታው ጥሩ ያልነበረው አምበሉ ጋቶች ፓኖም ብቻ ነበር። ጋቶች ጥሩ ያልተጫወተ መሆኑን የተመለከቱ ጋዜጠኞች አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲችን በቦታው ከጋቶች ይልቅ መስዑድ መሀመድን ለምን እንዳላሰለፉት ጠይቀዋቸው ነበር። አሰልጣኙ ሲመልሱም መስዑድን ያላሰለፉት በድካም ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል። ሆኖም ከአንዳንድ የመረጃ ምንጮች በደረሰን መረጃ ግን አሰልጣኝ ፖፓዲች መስዑድን ያላሰለፉት ተጫዋቹ ስለደከመ ሳይሆን ማጫወት ስላልፈለጉ ነው።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ37 ነጥብ መሪነቱን ሲያጠናክር ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በአስር ነጥብ ዝቅ ብሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

በሌሎች ጨዋታዎች አዳማ ከነማ በታፈሰ ተስፋዬ ብቸኛ ጎል አርባምንጭ ከነማን አንድ ለባዶ ሲያሸንፍ ወደ ሆሳዕና ያቀናችው መሰረት ማኔ ሀድያ ሆሳዕናን ሁለት ለባዶ አሸንፋ ተመልሳለች። ለድሬዳዋ ከነማ ጎሎቹን ያስቆጠሩት ሱራፌል ዳንኤል እና በቅርቡ ከአሜሪካ መጥቶ ድሬዳዋን የተቀላቀለው ፉአድ ኢብራሂም ናቸው። ባለፈው ሳምንት ፈረሰኞቹን አንድ ለባዶ ያሸነፈው የመሰረት ማኔው ድሬዳዋ ከነማ ከተከታታይ ድል በኋላ ደረጃውን ወደ አራት ማሳደግ ችሏል። አዳማ ከነማ በበኩሉ ነጥቡን 30 አድርሶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በደቡብ ደርቢ ቦዲቲ ላይ የተገናኙት ወለይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል። 

ሊጉ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ንግድ ባንክ ከሀዋሳ ከነማ እንዲሁም በቅርቡ ብሔራዊ ቡድኑን ለማሰልጠን እንደተስማማ የሚነገርለት ገብረመድኅን ሀይሌ መከላከያን ይዞ ዳሽን ቢራን ያስተናግዳል።

ሊጉን ፈረሰኞቹ በ37 ነጥብ ሲመሩ ከመሪው በ30 ነጥብ የሚያንሰው ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ታፈሰ ተስፋዬ 11 ጎሎችን በማግባት ኮከብ ጎል አግቢነቱን ሲመራ አዳነ ግርማ እና ያቡን ዊሊያም በእኩል ዘጠኝ ጎሎች ይከተሉታል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
afrasa [652 days ago.]
 we told u before Adama&Diredawa will rule the league in a couple of years

arachni_name) [63 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text)

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!