ሳናከብረው ያስከበረን የኩራታችን ምንጭ “ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ”
ግንቦት 09, 2008

ሳናከብረው ያስከበረን የኩራታችን ምንጭ “ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ”
በይርጋ አበበ

ባርሴሎና 1984 ዓ.ም ታላቁን የስፖርት ውድድር የበጋ ኦሎምፒክ አዘጋጀች። ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳተፈች። አንዲት ጠይም ቆንጆ ልጃገረድ ቀጫጭን እግሮቿ ሩጣ 25 ዙር የሚሸፍነውን ሩጫ ስትጨርስ የቀደማት አልነበረም። አብረዋት የተሰለፉት በሙሉ እሷን ተከትለው ገቡ።

ይህች ሴት ደራርቱ ቱሉ ነች። ደራርቱ በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ስታስገኝ ሁለት ታሪኮችን ሰርታ ነበር። ኦሎምፒክን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት የሚለው አንዱ ሲሆን ሁለተኛውና ትልቁ ታሪክ ደግሞ ይህ ድሏ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ መሆኑ ነው። 

 

ከላይ በመግቢያዬ ላይ ከጠቀስኩት ታሪክ ጀርባ አንድ ጎልማሳ አሉ። ይህ ጎልማሳ ሰው ውጭ አገር ቆይቶ አዲስ አበባ ሲገባ ወይም የሚያሰለጥናቸው ልጆች ካላሸነፉ ፊቱ የማይፈታ ኮስታራ ሰው ነው የኮስትሬ ልጅ ወልደመስቀል ኮስትሬ። ደራርቱ ለአፍሪካም ሆነ ለአገሯ የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት የሆነችበትን ታሪክ ስታስመዘግብ ትልቁን የቤት ስራ የሰሩት እኒህ ጎልማሳ ናቸው። 

ከዚህ ድል በኋላ በ1996 አትላንታ ላይ ሀይሌ ገብረሥላሴ በተመሳሳይ ርቀት የወርቅ ባለቤት ሲሆን አሰፋ መዝገቡ የነሃስ ሜዳሊያውን ይዞ ወደ አገሩ ተመለሰ። በዚህ ጊዜም እኒህ ጎልማሳ ከድሉ ጀርባ አሉ። ሲድኒ ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ይስታገኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ የሶስቱ ወርቆች መገኛ ውድ የማዕድን ቦታ ናቸው። በአጠቃላይ በአምስት የኦሎምፒክ ውድድሮች የ10 እና አምስት ሺህ ሜትር ሯጮችን ይዘው አገራቸውን የመሩት አዛውንቱ ወልደመስቀል ኮስትሬ 13 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያስመዘገቡ ሲሆን 15 ብርና ነሃስ በድምሩ 28 የወርቅ ሜደዳሊያዎችን ለአገራቸው አስመዝግበዋል። 

ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከአትሌቲክሱ ድላቸው በተጨማሪ በእግር ኳስ ተጫዋችነታቸውና አሰልጣኝነታቸው ውጤታማ የነበሩ ቢሆንም በስፋት ታዋቂ የሆኑት ግን በአትሌቲክስ አሰልጣኝነታቸው ነው። ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ስትሆን እኒህ ሰው ለአገራቸው ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ባለውለታ ሆኑ ማለት ነው። ዳሩ የሚውልባትን እንጂ የሚውልላትን የማታከብረው ኢትዮጵያ ይህን ትልቅ የኩራትና የክብር ምንጯን ሳታከብር ሸኘችው። ባለቅኔው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ

“አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ”


 ያለው ለእኒህ አዛውንት ይሆን? 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Teferi [313 days ago.]
 13 gold medals + 15 bronze is not equal to 28 gold medals

teshe [311 days ago.]
 i laike. it is the best of best

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!