የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላትን ሸለመ
ግንቦት 11, 2008

በይርጋ አበበ የሶማሊያ አቻውን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈውና ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ለማጣሪያ የሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከፌዴሬሽኑ ሽልመት ተበረከተለት። ሽልማቱን ያበረከቱት የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ መሆናቸውንም ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

ለእያንዳንዱ የቡድኑ አባላት አስር አስር ሺህ ብር የሸለመው ፌዴሬሽኑ በድምሩ 320 ሺህ ብር ወጭ ማድረጉንም አስታውቋል። ሽልማቱን ያበረከቱት አቶ ተክለወይኒ “እናንተ በግላችሁ አሸናፊ ነኝ በቡድንም እናሸንፋለን የማለት ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል። ከፊት ለፊታችሁ የሚጠብቃችሁ ጠንካራው የጋና ብሔራዊ ቡድነ ነው። እሱን አሸንፋችሁ ለአፍሪካ ዋንጫ እንደምትበቁ እምነቴ ነው። ይህ የገንዘብ ሽልማት በቂ እንዳልሆነ እናውቃለን ነገር ግን ላለፈው ስራችሁ እውቅና ነው” ማለታቸውን ዘጋቢያችን በላከልን መረጃ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ፌዴሬሽኑ ቡድኑን በኢትዮጵያ ሆቴል የሽልማት ስነ ስርዓት ባካሄደበት ወቅት በቦታው የተገኙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ተቋማት ውስን መሆን አነጋጋሪ ሆኗል። በታዳጎዎች ላይ እንሰራለን እየተባለ ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሚሸለምበት እለት በስፍራው የተገኙ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ውስን መሆናቸው የቡድኑን አባላትም እንዳስከፋ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር በደርሶ መልስ እንዲጫወት እጣ የደረሰው ሲሆን ማሸነፍ ከቻለ ወደ ውድድሩ የሚያቀና ይሆናል።

በተያያዘ ዜና በፊፋ እና በካፍ የክለብ ላይሰንሲነግ ዓለም አቀፍ ሴሚናር በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን በሂልተን ሆቴል መግለጫ ይሰጣል። ከፌዴሬሽኑ የተላው መግለጫ ሙሉ ቃል ˝በአለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማህበር /ፊፋ / እና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን / ተባባሪነት የተዘጋጀው  የከለብ ላይሰንሲንግ ዓለም ዓቀፍ ሴሚናር ግንቦት 11 እና 12/2008 በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡በሴሚናሩ ከ12 ሀገሮች የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የተውጣጡ  ከ40 በላይ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡የሴሚናሩን አጠቃላይ ዓላማዎች እና የመጀመሪያ ቀን ውሎ በማስመልከት ነገ ግንቦት 11/2008 ዓ.ም በ12፡00 በሂልተን ሆቴል ጋዜጣዊ መገላጫ ተዘጋጅቷል˝ ሲል ይገልጻል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!