ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ጋናን ይገጥማ
ግንቦት 13, 2008

በይርጋ አበበ

የወጣቶች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በማጣሪያ ዝግጅት ላይ የሚገኘውና በቅርቡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በነብስ ወከፍ የአስር ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተለት ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታል። ጨዋታው የሚካሄደውም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ነው። 

በኢትዮጵያ በኩል ሁኩም የቡድኑ አባላት በበቂ ዝግጅትና ጤንነት ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከሶከር ኢትዮጵያ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነውም መጠነኛ ጉዳት ላይ የነበረው አጥቂው አሚ መሃመድ ከጉዳቱ አገግሞ ልምምድ ሰርቷል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታው የሶማሊያን ብሔራዊ ቡድን አዲስ አበባ ላይ ሁለት ለአንድ እና ጂቡቲ ላይ ደግሞ ሁለት ለባዶ በድምሩ አራት ለአንድ በማሸነፍ ነበር ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ለመጫወት የበቃው። ከጋና ጋር በሚያደርገው የ180 ደቂቃ ፍሚያ በለስ ከቀናው ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚያቀና ይሆናል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!