አሚ መሀመድ የነገሰበት ጨዋታ እና የወጣት ብሔራዊ ቡድን ጉዞ
ግንቦት 14, 2008

በይርጋ አበበ

ትናንት ከቀትር መልስ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር ተጫውቶ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ደግሞ ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ ያመሸው የጂማ አባቡና እግር ኳስ ክለብ አጥቂ የሆነው አሚ መሀመድ ነው።

ወጣቱ አጥቂ ብሔራዊ ቡድኑ ለድል የበቃባቸውን ሁለት ጎሎች በአምስት ደቂቃዎች ልዩነት ከማስቆጠሩም በላይ በተለይ ከእረፍት በፊት በነበረው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የጨዋታው ኮከብ የሚያስብለውን ብቃት ማሳየት ችሏል። ከጨዋታው በኋላ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የጋናው ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝም ቢሆን ያረጋገጡት የልጁን ምትሃታዊ እግሮች  ብቃት አስተማማኝነት ነበር። የብሔራዊ ቡድኑን ብቃት በተመለከተም ቴክኒካል ብቃታቸው ጥሩ መሆኑን እና ወደ ፊት ጥሩ ቡድነ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው የገለጹት። በመልሱ ጨዋታ ቡድናቸው አሸንፎ እንደሚያልፍ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አቻቸው አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሀንስ በበኩላቸው ለድላቸው ተጫዋቾቻቸውን አድነቀዋል። አሰልጣኙ አያይዘውም ቡድናቸው ከጨዋታ ጨዋታ እየተዋሃደ መምጣቱን አስተውቀዋል። ለመልሱ ጨዋታም በተሻለ እንደሚዘጋጁ እና ለአፍሪካ ዋንጫው እንደሚበቁ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ኳስን ተረጋግቶ በመጫወት በኩል ክፍተት የታየ ሲሆን በተለይ በመሀል ሜዳው ክፍል ቡድኑን የሚያረጋጋ እና ኳስን በሚገባ የሚቆጣጠር አማካይ ተጫዋች ክፍተት መኖሩ ታይቷል። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ወጣቱ አጥቂ አሚ መሃመድ የጨዋታው ኮከብ እና ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋች ሆኖ አምሽቷል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [35 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!