አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የብሔራዊ ቡድን አባላቱን አሳወቀ
ግንቦት 15, 2008

በይርጋ አበበ

በቅርቡ ዋልያዎቹን ለማሰልጠን ከፌዴሬሽኑ ጋር ስምምነት ላይ የደረሰው ገብረመድህን ሀይሌ 23 የቡድኑን አባላት ስም ዝርዝር ለፌዴሬሽኑ አስታውቋል። በአሰልጣኙ ምርጫ ኢትዮጵያ ቡና አምስት ተጫዋቾችን በማስመረጥ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት አስመርጧል። ከመከላከያ ሁለት ከሲዳማ ቡና ሁለት ከዳሽን ቢራ እንዲሁም ከደደቢት ሁለት ተጫዋቾች ሲመረጡ ከንግድ ባንክ ከሀዋሳ ከነማ ከአርባ ምንጭ ከነማ እና ከድሬዳዋ ከነማ አንድ አንድ ተጫዋቾች ሲመረጡ ከሱፐር ሊጉ ደግሞ ሙገር ሲሚንቶ አንድ ተጫዋች አስመርጧል። በአሰልጣኙ ምርጫ የመከላከያው ባዬ ገዛኸኝ አለመካተቱ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ አይን የገቡት 23ቱ ተጫዋቾች ስም ዝርዝር እነሆ

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው ከመከላከያ
አቤል ማሞ ከሙገር ሲሚንቶ
ሳምሶን ጥላሁን ከድሬደዋ ከነማ

ተከላካዮች

ኤፍሬም ወንድወሰን ከኢትዮጵያ ቡና
አብዱልከሪም መሃመድ ከኢትዮጵያ ቡና
አህመድ ረሺድ ከኢትዮጵያ ቡና
አንተነህ ተስፋዬ ከሲዳማ ቡና
ያሬድ ባዬህ ከዳሽን ቢራ
ስዩም ተስፋዬ ከደደቢት
አዲሱ ተስፋዬ ከመከላከያ
አስቻለው ታመነ ከቅዱስ ጊዮርጊስ

አማካይ መስመር

ምንተስኖት አዳነ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
ኤሊያስ ማሞ ከኢትዮጵያ ቡና
በሀይሉ አሰፋ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
ታደለ መንገሻ ከአርባ ምንጭ ከነማ
አስራት መገርሳ ከዳሽን ቢራ
ሙሉዓለም መስፍን ከሲዳማ ቡና
ጋቶች ፓኖም ከኢትዮጵያ ቡና

አጥቂዎች

ሳላዲን ሰይድ ከቅዱስጊዮርጊስ
ደስታ ዮሀንስ ከሀዋሳ ከነማ
ኤፍሬም አሻሞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
 ታፈሰ ተስፋዬ ከአዳማ ከነማ
ዳዊት ፈቃዱ ከደደቢት ናቸው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!