ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለ37 ፕሮጄክቶች ድጋፍ አደረገ
ግንቦት 18, 2009

በይርጋ አበበ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በታዳጊዎች እግር ኳስ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኘው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ሰሞኑን በታዳጊዎች እግር ኳስ ላይ የሚያተኩር “የዳሽን አርሴናል የታዳጊዎች አሰልጣኞች ስልጠና” ሶስተኛ ዙርር ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው 37 የፕሮጀክት አሰልጣኞች መሳተፋቸውን ክለቡ አስታውቋል። ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተሰጣው ስልጠና ከተጠናቀቀ በኋላ ዳሽን ቢራ እነዚሁ አሰልጣኞች ለሚያሰለጥኗቸው ታዳጊዎች የሚሆኑ 250 ኳሶችን ጨምሮ ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። 

Dashen Beer


ከዳሽን ቢራ በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ስልጠናውን የሰጡት ከአርሴናል እግር ከስ ትምህርት ቤት የመጡ ሁለት አሰልጣኞች ሲሆኑ አሰልጣኞቹ ከስልጠናው በኋላም “ፕሮጀክቶችን ስንጎበኝ ስልጠናው ያመጣቸውን ለውጦች በተወሰነ መልኩ ተመልክተናል፤ በተለይ ደግሞ አሰልጣኞች እንዴት ማሰልጠን እንዳለባቸው ሳይሆን እውቀታቸውን እንዴት መተግበር እንዳለባቸው እያሰለጠናቸው ስለሆነ ይህን እየተገበሩ መሆኑን ለመገንዘብ ችያለናል። ወደፊትም ከስልጠናው ብዙ ስኬት እንደሚገኝ ተስፋ እናደርጋለን” ብሏለዋል።

ስልጠናውን ለተከታተሉት 37 የፕሮጄክት አሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የሰጡት የፋብሪካው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መክብብ አለሙ ሲሆኑ እሳቸውም “የዳሽን -አርሰናል ተከታታይ የታዳጊዎች እግር ኳስ አሰልጣኝነት ስልጠና ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ አዳዲስ አሰልጣኞች እንዲሳተፉበ ግል፣ በእግር ኳስ ፌደሬሽን እና በክልል ስፖርት ኮሚሽኖች ጥያቄ በመቅረቡ አዲስ 15 ሰልጣኞች በዚኛው ዙር ተካተዋል" ብለዋል።አቶ መክብብ አክለውም “ይህም የስልጠናው ስኬት ማሳያነው፤ ዳሸን ቢራም በቀጣይ የሀገሪቷን እግርኳስ የሚያሻሽሉ ስራዎቹን አጠናክሮ ይቀጥላል” በማለት ተናግረዋል።
ዳሽን ቢራ ከእንግሊዙ ታላቅ ክለብ አርሴናለ ጋር በገባው የሶስት ዓመታት ውልም መሰረት ከአርሴናል ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እያስመጣ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ እና ስልጠናም እንዲሰጡ እያደረገ ሲሆን የአሁኑ ስልጠና ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው። ቢራ ፋብሪካው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚወዳደር ክለብ ቢኖረውም እና ለክለቡ በርካታ ገንዘብ ቢመድብም የክለቡ የሜዳ ውጤት ግን ከእጅ ወደ አፍ እንደሆነ የደሃ ገበሬ ኑሮ አይነት በየዓመቱ ላለመውረድ የሚዳደር ክለብ ነው። ፋብሪካው በታዳጊዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ቢሆንም ክለቡ ግን ታዳጊ ቡድን የለውም።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!