ከአፍሪካ እግር ኳስ ስኬታማ ሰዎች መካከል አንዱ ዛሬ ተሸኘ
ሰኔ 01, 2008

ከአፍሪካ እግር ኳስ ስኬታማ ሰዎች መካከል አንዱ ዛሬ ተሸኘ

በይርጋ አበበ

የናይጄሪያ እግር ኳስ በአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ ደረጃ ከሚሰጣቸው ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን የአገሪቱ እግር ኳስ በታሪኩ በአህጉሩ ላይ የነገሱ የእግር ኳስ ጠበብቶችን ከማፍራት የቦዘነበት ዘመን አልነበረም። በተለይ ናይጄሪያ በ1970ዎቹ እና 80ዎቹ እንዲሁም 1990ዎቹ የነበራት የበላይነት ከፍተኛ ነበር።

በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የናይጄሪያ እግር ኳስ ለዓለም ካበረከታቸው ክዋክብት መካከል አንዱ ዛሬ በሞት የተሰናበተው ስቴፈን ኬሽ ይገኝበታል። ኬሽ የናይጄሪያን ብሔራዊ ቡድን ለረጅም ዘመናት በተጫዋችነት ያገለገለ ሲሆን ቡድኑን በአምበልነት እየመራም ስኬታማ ዘመናትን ማሳለፍ ችሏል። ይህ ስኬታማ ተጫዋች ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ሲገለል ደግሞ በአሰልጣኝነት የተለያዩ አገራትን እና ክለቦችን ማሰልጠን ችሏል።

የቶጎን ብሔራዊ ቡድን እየመራ ለዓለም ዋንጫ ያበቃው ናይጄሪያዊው ኬሽ የአገሩን ብሔራዊ ቡድን እየመራ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በመቅረብም የውድደሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። በግሉም የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝነት ክብርን መጎናጸፍ ችሎ ነበር። ስቴፈን ኬሽ በደመወዝና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ከናይጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በተለይ የደቡብ አፍሪካን ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ውስጥ ውስጡን ተስማምቷል መባሉን ተከትሎ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቶ ነበር ከፌዴሬሽኑ ጋር። የቶጎን ብሔራዊ ቡድን በሚያሰለጥንበት ወቅትም ቢሆን ከቡድኑ አምበል ኢማኑኤል አዲባዮር ጋር እንካ ሰላምታ ውስጥ ገብቶ እንደነበር የተለያ መገናኛ ብዙሃን ደጋግመው ዘግበውት ነበር።

በአሰልጣኝነትና ተጫዋችነት ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ስቴፈን ኬሽ የናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ኮከብ የእግር ኳስ ሰው ነበር። ስኬታማው ተጫዋችና አሰልጣኝም ትናንት በ54 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ኬሽ እና ኢትዮጵያ በ2013

2013 ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የመነቃቃት ዘመን ነበር ማለት ይቻላል። ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመራ የሱዳንን ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ አሸንፎ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈበት ዘመን ሲሆን በቻን ውድድርም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለፈበት ዘመን ነበር። ብሔራዊ ቡድናችን በተጠቀሰው የውድድር ዓመት ያስመዘገባቸው ስኬቶች እንዳሉ ሆኖ በተጓዳኝ ደግሞ በመጥፎ ሊነሳ የሚችለው የቡድኑ ታሪክ ከናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ አለመቻሉ ነው።

በስቴፈን ኬሽ ይመራ የነበረው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስብስብ ጋር የተገናኘው በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ነበር። በወቅቱ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ጨዋታ ናይጄሪያዎች ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችለው ነበር። ሁለቱንም ጎሎች ያስቆጠረው ቪክቶር ሞሰስ ሲሆን ጎሎቹም በፍጹም ቅጣት ምት የተገኙ ነበሩ።

ብራዚል ላዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የአቶ ሰውነት ቢሻው ስብስብ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ሲደርስ የተገናኘው ከናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድነ ጋር ሲሆን በደርሶ መልስ በተካሄደ ጨዋታም ኬሽ አራት ለአንድ ማሸነፍ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሁለቱ አገሮች ናይጄሪያ ላይ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ አሁንም የኬሽ ስብስብ ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። በዚህ ጨዋታ ናይጄሪያዎች ከመስመር በእጅ የወረወሩት ኳስ የጀማል ጣሰውን እጆች አልፋ የተቆጠረች ጎል አንዷ ናት።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!