ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ሲያጠናክር ታፈሰ ተስፋዬ የኮከብ ጎል አግቢነቱን ልዩነት ማስፋት ችሎአ
ሰኔ 08, 2008

ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ሲያጠናክር ታፈሰ ተስፋዬ የኮከብ ጎል አግቢነቱን ልዩነት ማስፋት ችሎአል

ይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መሪሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በተስፋዬ አለባቸው ብቸኛ ጎል በማሸነፍ ነጥቡን ከተከተዩ አዳማ ከነማ ጋር በነበረበት እንዲቀጥል አድርጎአል!! ፈረሰኞቹ ንግድ ባንክን በማሸነፋቸው ነጥባቸውን 48 በማድረስ ከተከታያቸው ጋር ያላቸውን ልዩነት ዘጠኝ በማድረስ የሻምፒዮናት እድላቸውን አስፍተዋል!! በቀጣዩ ጨዋታቸው አንድ ነጥብ ማግኘት ከቻሉ ሻምፒዮን ይሆና!!

በሌላ ዜና ትናንት ወደ ሆሳዕና ያቀናው አዳማ ከነማ በታፈሰ ተስፋዬ ሁለት ጎሎች ሀድያ ሆሳዕናን ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ችሎአል!! ታፈሰ ትናንት ያስቆጠራቸውን ጎሎች ጨምሮ በዓመቱ ስቆጠራቸው ጎሎች ብዛት 13 ደርሰውለታል!! ለሆሳዕና ብቸኛዋን ጎል ያስቆጠረው አምሬላ ዴልታታ ነው!!

ወላታ ድቻ አሁንም በኣቻ ውጤት እንዲገፋ ደረገውን ውጤት አስመዝግቦአል!! ከመከላከያ ጋር ቦዲቲ ላይ የተጫወተው ወላይታ ድቻ በአላዛር ፋሲካ አማካኝነት አንድ ጎል ቢያስቆጥርም ለመከላያ ተከላካዩ ቴዎድሮስ በቀለ ባስቆጠራት ጎል ነጥብ ተጋርቶ መውጣት ችሎአል!!

የሊጉ ቀሪ አራ ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ተሞች የሚካሄዱ ሲሆን ከኢትዮጵያ ቡና በፎርፌ ሶስት ነጥብ ያገኘው ሀዋሳከነማ በሜዳው ደደቢትን ሲያስተናግድ ፎርፌ ቅጣት የተከናነበው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማ ቡናን ይገጥማል!! ድሬዳዋ በሜዳው የመውረድ ስጋት ያንዣበበበትን ኤሌክትሪክን የሚያስተናግድ ሲሆን የሁለት ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ጨዋታ ቅጣት የተላፈበት ዳሽን ቢራ በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታየም አርባምንጭ ከነማን ይገጥማል!! የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ላመውረድ የሚደረግፍልሚያ በመሆኑ ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይተበቃ!! አራም ጨዋዎች የሚካሄዱት በተመሳሳይ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነው!!  


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
champ [312 days ago.]
 'አራም ጨዋዎች' Please check ur spelling.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!