የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ቡና ላይ በአይነቱ ከባድ የሆነ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ
ሰኔ 08, 2008

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ቡና ላይ በአይነቱ ከባድ የሆነ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ  

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ እግ ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከሀዋሳ ከነማ አቻው ጋር ባደረገው የፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጨዋታ ላይ ደጋፊዎች ባሳዩት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ባህሪ ምክንያት የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ፌዴሬሽኑ አስታወቀ።

የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ እንዳስታቀው ኢትዮጵያ ቡና እግ ኳስ ክለብን በሀዋሳ ከነማ ጨዋታ የፎርፌ ቅጣት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን በቀጣይም ለአንድ ዓመት ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር እንዲታገድ መወሰኑን አስታውቋል። ነገር ግን ሁለተኛውና ከባድ ውሳኔ የተባለው ክለቡን ለአንድ ዓመት የመቅጣት ውሳኔው ተፈጻሚ የሚሆነው የክለቡ ደጋፊዎች በቀጣይ ተመሳሳይ ባህሪ የሚያሳዩ ከሆነ ብቻ መሆኑን የገለጸው የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በዚህም ምክንያት ለቀጣዩ ዓመት ውሳኔው ሳይፈጸም እንደሚቆይ አስታውቋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ እና ከድሬዳዋ ከነማ ጋር በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲያካሂድ ያስተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጿል።  

በሌላ ዜና በኢትዮጵያ ቡና እና በሀዋሳ ከነማ ጨዋታ ወቅት በተፈጠረው ብጥብጥ ምክንያት ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የአንድ መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ቀጣት እንዲከፍልም ተወስኖበታል። 

 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bikila [584 days ago.]
 ahun beza balefew gonder lay tenagrenal buna yemibal kileb sayihon yashebariwoch guday asfetsami biba;l yishalal. lenegeru fikadu dergm ayidel ende. beguaro ber gebito new enji. ahunm chikchik yelelew kitat yasifeligal . medeawum arfo yikemet yestadium wubet yebuna degafi eyal;u gazetachew endishet yemilefelifu yesport gazetegnoch sirat yiyazu. beka sport lewedajinet enji tor meda kehone endesemonu yalshebabi weyim shabiya begilts tornet jemiru bunawoch . ende beza astela eko shem new .

arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!