ኤሌክትሪክ ደረጃውን ሲያሻሽል ድሬዳዋ ወደ ወራጅ ቀጠናው ተንደረደረ
ሰኔ 09, 2008

ኤሌክትሪክ ደረጃውን ሲያሻሽል ድሬዳዋ ወደ ወራጅ ቀጠናው ተንደረደረ

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት በተመዘገቡ ውጤቶች ዳሽን ቢራን ወደ ወራጅ ቀጠናው ሲያንደረድረው ኤሌክትሪክን ደግሞ ላለመውረድ የሚያደርገውን ጥረት ተስፋ የሰጠ ሆኗል። ትናንት ከቀትር መልስ በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም የተገናኙት ሁለቱ የመውረድ ስጋት ያጠላባቸው ዳሽን ቢራ እና አርባ ምንጭ ከነማ ሁለት እኩል በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን ጨርሰዋል። በዚህም መሰረት አርባ ምንጭ ነጥቡን ወደ 27 ከፍ በማድረግ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንጻሩ ዳሽን ቢራ 24 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል።

ሌላው የመውረድ ስጋት አፍንጫው ስር አድብቶ የሚጠብቀው ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በፍጹም ገብረማሪያም ብቸኛ ጎል አንድ ለባዶ በማሸነፍ ለጊዜውም ቢሆን ደረጃውን በአንድ ማሻሻል ችሏል። 12 የጎል እዳዎችን የተሸከመው ኤሌክትሪክ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ትናንት በኤሌክትሪክ በሜዳው የተሸነፈው ድሬዳዋ ከነማ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ተከታታይ ሽንፈቶችነ እያስተናገደ በመሆኑ 30 ነጥቦችን ይዞ 10ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገድዷል።

ሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ከተጀመረ በኋላ ማሸነፍ ተስኖት የቆየውና ባለፈው ሳመንት በዳሽን ቢራ ላይ የጎል ናዳ ያወረደው  ደደቢት ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል። ደደቢት በዳዊት ፈቃዱ እና በሳሙኤል ሳኑሚ አማካኝነት ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ባለሜዳው ሀዋሳ ከነማ በበኩሉ በአስቻለው ግርማ እና በሙጂብ ቃሲም አማካኝነት ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ሰሞኑን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የቅጣት ናዳ የወረደበት ኢትዮጵያ ቡና ወደ ይርጋለም አቅንቶ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ ባዶ ለባዶ በመለያየት ተመልሷል።

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ48 ነጥብ ሲመራ አዳማ ከነማ በ39 ይከተለዋል። ከፍተኛ ጎል አግቢነቱን ደግሞ ታፈሰ ተስፋዬ ከአዳማ ከነማ በ13 ይመራዋል። ዳዊት ፈቃዱ ከደደቢት 11 ጎሎችን ይዞ ይከተላል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!