እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልዋሎ አዲግራት ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለ
ሐምሌ 01, 2008

እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልዋሎ አዲግራት ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

በይርጋ አበበ

ትናንት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው በሲፐር ሊጉ የሚወዳደረው የትግራይ ክልሉ ተወካይ “ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ክለብ” ከፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት ተላልፎበታል።

ክለቡ የተላለፈበት የቅጣት ወሳኔ 30 ሺህ ብር እና ሶስት ጨዋታዎችን ከሜዳው ውጭ እንዲጫወት የሚል ሲሆን ወልዋሎ ለዚህ ቅጣት የተዳረገው መቀሌ ከነማ ከፋሲል ከነማ ጋር አዲግራት ላይ ባደረጉት ጨዋታ ደጋፊዎቹ ባሳዩት ያልተገራ ባህሪ ምክንያት መሆኑን ፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።

መቀሌ ከነማ እና ፋሲል ከነማ መቀሌ ላይ መጫወት ሲገባቸው አዲግራት ላይ እነዲጫወቱ የተዳረገው በመቀሌ ደጋፊዎች አመለ ብልሹነት ቢሆንም የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እና እግር ኳስ ተጫዋቾች አዲግራት ላይም ያልተገሩ ደጋፊዎች ሰለባ ከመሆን አልዳኑም። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አንስቶ ጨዋታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የወልዋሎ ደጋፊዎች በፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ላይ የስድብ ናዳ ሲያወርዱባቸው እንደነበር የገለጸው የፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላም ቢሆን ተጫዋቾቹን ከሜዳ አናስወጣም ብለው በድንጋይ የመማታት ሙከራ ማድረጋቸውንም ገልጿል። ሆኖም በጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ትብብር ለሁለት ሰዓታት የተጠጋ ጊዜያትን ከሜዳ እንዳይወጡ የተዳረጉት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በፖሊስ ታጅበው ከሜዳ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ከሜዳ ከወጡ በኋላም ወደ ቀያቸው የተመለሱት በፖሊስ ታጅበው መሆኑንም ተገልጿል።

ይህን መሰል ለእግር ኳሱ ነቀርሳ ድርጊት የፈጸሙት የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ደጋፊዎች ክለባቸውን ለ30 ሺህ ብር እና በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት ቅጣት እንዲከናነብ ምክንያት ሆነውበታል። በቀጣይም ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ክለቡ ከፍተኛ ቅጣት እነደሚጠብቀው ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ባህር ዳር ላይ ባህር ዳር ከነማ እና መቀሌ ከነማ ሲጫወቱ መቀሌ ከነማ ጎል ሲቆጠርባቸው ዳኛውን ከመደባደባቸውም በላይ አንጫወትም ብለው ለ45 ደቂቃ ተለምነው መግባታቸውን ከባህር ዳር ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!