መሰረት ማኔን ያሰናበተው ድሬዳዋ ከተማ ዮርዳኖስ አባይን ሊቀጥር ነው
ሐምሌ 06, 2008

መሰረት ማኔን ያሰናበተው ድሬዳዋ ከተማ ዮርዳኖስ አባይን ሊቀጥር ነው

በይርጋ አበበ

ድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለአራት ዓመታት በብሔራዊ ሊጉ ሲዋዥቅ ከከረመ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለስ ያስቻለችውን አሰልጣኝ መሰረት ማኔን ከእነረዳቷ ማሰናበቱን ባሳለፍናቸው ሁለት ሳመንታት አስታውቋል። በመሰረት ምትክም ሌላውን ታሪካዊ ተጫዋች ዮርዳኖስ አባይን ሊቀጥር መስማማቱ እየተነገረ ነው።

በየዓመቱ በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ላይ በክብር እንግድነት ተጠርታ ወደ ስፍራው ያመራችው አሰልጣኝ መሰረት ማኔ ክለቧን ድሬዳዋ ከነማን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካሳደገች በኋላ በመጀመሪያው የውድድር ዙር ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን ብታስችለውም በሁለተኛው ዙር ክለቡ ባሳየው የወረደ አቋም ምክንያት ለስንብት እንደዳረጋት ተነግሯል። በመጀመሪያው ዙር አምስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከነማ በዓመቱ መጨረሻ ግን 11ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የክለቡን ኃላፊዎች እንዳስቆጣቸው ተነግሯል። መሰረት ማኔ በአፍሪካ ብቸኛዋ እና የመጀመሪያ ሴት የትልቅ ክለብ አሰልጣኝ መሆኗ ይታወቃል።

ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ድሬዳዋ ከነማን የተቀላቀለው አጥቂው ዮርዳኖስ አባይ ለድሬዳዋ ከነማ አንድ ጎል ብቻ አስቆጥሮ የውድድር ዓመቱን መጨረሱ ይታወቃል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!