ፍሬው ሰለሞን እና ኤፍሬም አሻሞ ወደ ሲዳማ ቡና?
ሐምሌ 06, 2008

ፍሬው ሰለሞን እና ኤፍሬም አሻሞ ወደ ሲዳማ ቡና?

በይርጋ አበበ

ከመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ጋር ሰኬታማ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው አማካዩ ፍሬው ሰለሞን እና ከአሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማሪያም ጋር ከክለብ ክለብ የሚሽከረከረው እየተባለ የሚነገርለት ኤፍሬም አሻሞ ለሲዳማ ቡና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀረበላቸው። ከሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው የክለቡ አመራሮች ሁለቱንም ተጫዋቾች በማስፈረም በቀጣዩ የውድድር ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ እቅድ መያዙን ሰምተናል።

ሲዳማ ቡና ለሁለቱ ተጫዋቾች መጠኑ ዳጎስ ያለ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንደሚያቀርብ የገለጹት ምንጮቻችን በሁለቱ ተጫዋቾች የጨዋታ ሚና አመራሮቹ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸውልናል።

ፍሬው ሰለሞንም ሆነ ኤፍሬም አሻሞ ከክለቦቻቸው ጋር ያላቸው ኮንትራት ባሳለፍነው ሰኔ 30 የተጠናቀቀ መሆኑ ሲዳማ ቡና ተጫዋቾቹን ለማግኘት አይቸገርም ተብሎ ቢባልም ከተጫዋቾቹ የተሰጠ ምላሽ ግን የለም።

በሌላ ዜና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ላላፉት ስድስት ዓመታት የቆየው አምበሉ መስዑድ መሃመድ ለተጨማሪ ዓመታት በክለቡ የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈረም ከክለቡ ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑ ተሰማ። አመለ መልካምና ለታዳጊዎች አርአያ የሚሆን እየተባለ የሚነገርለት መስዑድ መሃመድ በ2007 ዓ.ም የውድድር አጋማሽ ላይ ለዳሽን ቢራ ለመፈረም ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ውሳኔውን በመከለስ ከቡና ጋር ቆይቷል።

ባለፈው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ላይ ክለቡን ለማሰልጠን የመጡት ሰርቢያዊው ድራጋን ፖፓዲች በርካታ ተጫዋቾችን “አልፈልጋችሁም” ብለው ሲያሰናብቱ መስዑድ ላይ ባላቸው እምነት ምክንያት እንዲቆይ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዓመቱ መጨረሻም በቡና ማሊያ ጥሩ ብቃት ካሳዩ ጥቂት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ለመሆንም ችሏል። የሁለቱን ወገኖች የድርድር ዝርዝር ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!