የዝውውር ዜናዎች
ሐምሌ 18, 2008

የዝውውር ዜናዎች

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ክለቦች ለቀጣይ ዓመት ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። በተለይ ባለፈው ዓመት ከደጋፊዎች ስነ ምግባር ጋር በተያያዘ ከፌዴሬሽኑ የቅጣት በትር በርትቶበት የከረመው ኢትዮጵያ ቡና ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙም በላይ ውላቸው የተጠናቀቁትን ኤፍሬም ወንድወሰንን እና ኤሊያስ ማሞን ውላቸውን እንዲያድሱ አድርጓል። አስቻለው ግርማን እና ዮሀንስ በዛብህን ከሀዋሳ ከነማ እንዲሁም አብዱልከሪም ሀሰንን ከንግድ ባንክ ያስፈረመው ቡና ለአምስቱ ተጫዋቾች ዝውውር ወደ ሰባት ሚሊዮን ብር ወጭ እንዳደረገ ተዘግቧል። በተለይ ለኤሊያስ ማሞ አንድ ነጥብ አምስት እና ለአስቻለው ግርማ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት አምስት ሚሊዮን ብር ከታክስ ነጻ ክፍያ እንደተከፈላቸው ከክለቡ ውስጥ አዋቂዎች የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከፈረሰኞቹ ጋር ላለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታ ያደረገው ዳዋ ሁጤሳ ወደ አዳማ ከነማ ማምራቱን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። እንደ ድረ ገጹ ዘገባ ከሆነ አዳማ ከነማ ከዳዋ ሁጤሳ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ በቡና ጋር የተለያየውን ጥላሁን ወልዴን፣ የሀዋሳ ከነማውን ሙጂብ ቃሲምን እና ሄኖክ ካሳሁንን ያስፈረመ ሲሆን ለዓመታት ሲፈልገው የነበረውን ኤፍሬም ቀሬንም የግሉ ማድረጉ ተገልጿል።

ሀዋሳ ከነማ ደግሞ የቀድሞውን የአዳማ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይ የነበረውን ያሬድ ዝናቡን ከደደቢት አስፈርሟል።

 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!