ዋሊድ አታ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት
ሐምሌ 20, 2008

ዋሊድ አታ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት

በይርጋ አበበ

ነሐሴ መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋነጫ ማጣሪያ የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ሀዋሳ ላይ ከሲሸልስ አቻው ጋር ያካሂዳል። ለዚያ ጨዋታ እንዲረዳቸውም አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ 28 ተጫዋቾችን የጠረዩ ሲሆን ከተጠሩት ተጫዋቾች መካከል ለስዊድኑ ክለብ የሚጫወተው ተከላካዩ ዋሊድ አታ ይገኝበታል። የዋሊድ አጣማሪ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች አስቻለው ታመነ ከአሰልጣኙ ምርጫ ውጭ ሆኗል።

አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ጥሪ ካደረጉላቸው 28 ተጫዋቾች መካከል ሶስቱ ማለትም ዋሊድ አታ ሽመልስ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ ከአገር ውጭ የሚጫወቱ ሲሆን ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች ተክለማሪያም ሻንቆ እና አቤል ማሞ ደግሞ ከሱፐር ሊጉ የተመረጡ ተጫዋቾች ሆነዋል።

የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ያላስመረጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንጻሩ መሃሪ መናን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመረጥ አማካዩ ተስፋዬ አለባቸው እንዲሁም አጥቂዎቹ ሳላዲን ሰይድ እና በሀይሉ አሰፋም ከፈረሰኞቹ ተመርጠዋል። ከኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ተከላካዮቹ አብዱልከሪም መሀመድ እና አህመድ ረሺድ እንዲሁም አማካዮቹ ኤሊያስ ማሞ እና ጋቶች ፓኖም ተመርጠዋል። ደደቢት በበኩሉ ተከላካዩን ስዩም ተስፋዬን እና አጥቂዎቹን ሽመክት ጉግሳን እና ዳዊት ፈቃዱን ጨምሮ በቅርቡ ክለቡን የተቀላቀለው ኤፍሬም አሻሞን አስመርጧል።

ከመከላከያ ደግሞ አዲሱ ተስፋዬ ቴዎድሮስ በቀለ እና ጀማል ጣሰው ሲመረጡ አዳማ ከነማ በበኩሉ አጥቂውን ታፈሰ ተስፋዬን እና በቅርቡ ክለቡን የተቀላቀለውን ተከላካዩን ሙጂብ ቃሲምን አስመርጧል። አንተነህ ተስፋዬ እና አዲሱ ግደይ ከሲዳማ ቡና ታደለ መንገሻ እና እንዳለ ከበደ ከአርባ ምንጭ ከነማ አስራት መገርሳ ከዳሽን ቢራ ሳምሶን አሰፋ ከድሬዳዋ ከነማ አቤል ማሞ ከሙገር ሲሚንቶ እና ተክለማሪያም ሻንቆ ከአዲስ አበባ ከተማ ከአገር ውስጥ ክለቦች የተመረጡ ተጫዋቾች ናቸው።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [35 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [35 days ago.]
 arachni_text)

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!