መስዑድ መሀመድ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ከቡና ጋር ለመቆየት ተስማማ
ሐምሌ 26, 2008

መስዑድ መሀመድ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ከቡና ጋር ለመቆየት ተስማማ

በይርጋ አበበ

ላለፉት ስድስት ዓመታት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የቆየው አማካዩ መስዑድ መሀመድ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን ስምምነት ዛሬ ተፈራረመ። የክለቡ የህዝብ ግንኙት ክፍል ኃላፊ አቶ አለማየሁ ወንድሙ ለኢትዮፉትቦል በስልክ እንዳስታወቁት ተጫዋቹ እና ክለቡ ለሳምንታት ሲያካሂዱት የቆዩትን ድርድር ስምምነት ላይ አድርሰውታል ብለዋል።

ተጫዋቹ እንዲከፈለ የጠቀውን ገንዘብ ክለቡ ሲመለከተው እንደቆየ የገለጹት አቶ አለማየሁ አሁን በተጫዋቹ እና በክለቡ ላይ ስምምነት ስለተደረሰ መስዑድ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የቡና አምበል ሆኖ ይቆያል ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ቡና ያለበትን የአጥቂ ችግር ለመቅረፍ ዓይኑን በደደቢቱ ሳሙኤል ሳኑሚ እና በንግድ ባንኩ ፍሊፕ ዳውዝ ላይ ማሳረፉ የተገለጸ ሲሆን ሁለቱም ተጫዋቾች አሁን በውጭ አገር ለሙከራ ሂደዋል። የቀድሞ የክለቡ አምበል ዳዊት እስጢፋኖስ እንዲመለስ የሚደረገው ድርድርም በሂደት ላይ ሲሆን አስራት መገርሳ ከዳሽን ቢራ ጋር ያለውን ኮንትራት በስምምነት የሚያቋርጥ ከሆነም ማረፊያው ቡና እንደሚሆን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።   


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!