ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ ፈረሰ
ነሐሴ 07, 2008


በይርጋ አበበ

ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ዝቅተኛ ውጤት ሲያስመዘግብ የቆየው ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ መፍረሱን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ችለናል። ከአንድ ወር በፊት የክለቡን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑልን በስልክ አነጋግሮ የነበረው የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዘጋቢ “ክለቡ ይፈርሳል ወይስ አይፈርስም” የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። አቶ ልዑል ሲመልሱም ገና መውረዳችንን መች አወቅንና ከፌዴሬሽኑ ጋር እየተከራከርን ነው ያላግባብ የተቀማነውን ሶስት ነጥብ እንዲመልሱልን” ሲሉ ነበር የመለሱለት። አቶ ልዑል በወቅቱ ለዘጋቢያችን አያይዘውም “ስለ ክለቡ ቀጣይ ጉዞ በስራ አስፈጻሚ ተወስኖ የሚተላለፈውን ለመገናኛ ብዙሃን እናሳውቃለን” ብለውታል።

እንደ አስራት መገርሳ የተሻ ግዛው መስፍን ኪዳኔ እና ያሬድ ባየህ አይነት ኮከብ ተጫዋቾችን ያሰባሰበው ዳሽን ቢራ በዚህ ዓመት ባስመዘገበው እጅግ ደካማ ውጤት ምክንያት ወደ ሱፐር ሊጉ መውረዱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም በየዓመቱ ከ40 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ለክለቡ የሚመድበው ቢራ ፋብሪካው በክለቡ ከተጠቀመው ይልቅ የከሰረው ስለበለጠበት ለማፍረስ እንዳነሳሳው ተገምቷል።

የደሽን ቢራን መፍረስ ተከትሎ እንደ ያሬድ ባየህ እና አስራት መገርሳ አይነት የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች ከዳሽን ቢራ ለቀው ወደሚፈልጓቸው ክለቦች በነጻ የማምራት እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው። በዚህም መሰረት በተለይ አስርት መገርሳ በጥብቅ ወደ ሚፈልገው ኢትዮጵያ ቡና የማምራት ነጻነት ያገኛል። ከዳሽን ቢራ የመልቀቂያ ወረቀት ካገኘሁ ማረፊያዬ ቡና ነው ብሎ መናገሩን ከቡና ሰወች ቀደም ሲል ምተናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
tegneabebe [501 days ago.]
 MengzamI a.t

arachni_name) [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [32 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!